በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተማሪዎችን እገታ የሚያወግዙ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

325

ጥር ፣ 19/20121 (ኢዜአ) ሰልፉ በባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ወልዲያ፣ ደብረ ብርሃንና ሌሎች ከተሞች ከጠዋቱ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሰልፈኞቹ በዋና ዋና መንገዶች እየተዘዋወሩ አለአግባብ ታግተው እየተሰቃዩ የሚገኙ ታዳጊ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የተለያዩ መልዕክቶችን እያሰሙ የሚገኙት ሰልፈኞቹ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥና መንግስትም ተማሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ሊያሳውቅ እንደሚገባ አመልክተዋል።