የቀንድ ከብቶችን ከሀገር ለማስወጣት ሲሞክሩ የተገኙ 15 ተጠርጣሪዎች ተያዙ

88
ሁመራ፣ ጥር 19/2012 (ኢዜአ)  የቀንድ ከብቶችን በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞክሩ የተገኙ 15 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ተያዙ ። በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን  የሁመራ መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ ኮማንደር መሰለ ይመም ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት 104 የቀንድ ከብቶችን በኮንትሮባንድ  ከሀገር ለማስወጣት ሲሞክሩ ተደርሶባቸው ነው። ተጠርጣሪዎቹ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ታህታይ አድያቦ ወረዳ በኩል ወደ ውጭ ለማሻገር ሲሞክሩ የአካባቢው ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አካላት ባደረጉት ትብብር አዲዋእላ በተባለው ስፍራ መያዛቸውን  አመልክተዋል፡፡ የቀንድ ከብቶቹም በቁጥጥር ስር  ውለው  ተጠርጣሪዎቹ ለተጨማሪ ምርመራ ፖሊስ ጣቢያ  እንደሚገኙ ኮማንደር መሰለ አስታውቀዋል፡፡ በተጠርጣሪዎች የተገኘ 306ሺህ የውጭ  ገንዝብም በቁጥጥር ስር መዋሉን ጨምረው ገልጸዋል። ከሳምንት  በፊትም 66 የቁም ከብቶች በተመሳሳይ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞክሩ የተገኙ ሶስት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ኢዜአ በወቅቱ ዘግቧል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም