የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ውሳኔ አስተላለፈ

246
አዲስ አበባ ሰኔ 18/2010 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ውሳኔ አስተላለፈ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 12ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የተሻሻለውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማምሻውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ ምክር ቤቱ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቷ በተከሰተው ነባራዊ ሁኔታ ሳቢያ በ2010 መከናወን የነበረበት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምርጫ መከናወን አለመቻሉን አመላክቷል። በመሆኑም ምርጫ ተካሂዶ አዲስ ምክር ቤት እስከሚደራጅ ድረስ አሁን በሥራ ላይ ያለው ምክር ቤትና አስፈፃሚ አካል ተግባሩን እያከናወነ እንዲቀጥል አስፈላጊነቱ ታምኖበታል ሲል ገልጿል። ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁም ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ እንዲፀድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መደረጉንም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም