በትግራይ የፈጠራ ስራዎችን ላከናወኑ ወጣቶች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ

75
መቀሌ ሰኔ 18/2010 በትግራይ ክልል የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ላከናወኑ ስድስት ወጣቶች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ፡፡ በመቀሌ ከተማ ትናንት በተከናወነው የሽልማት ስነስርዓት የትግራይ ክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ከ345 ሺህ ብር በላይ ለወጣቶቹ በማበረታቻነት አበርክቷል፡፡ በክልሉ የዓመቱ ምርጥ ተሸላሚ ከሆኑት መካከል የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ወጣት አሰፋ ተአምር አንዱ ነው። ወጣቱ ለሽልማት የበቃው በአስፋልት መንገዶች ላይ በተገነቡ የፍሳሽ ማስወገጃ ቀዳዳዎች ላይ ተገጥሞ ፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻን በመለየት ቀዳዳዎቹ በጎርፍ ምክንያት እንዳይደፈኑ ለመከላከል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ፈጥሮ ጥቅም ላይ በማዋሉ ነው። የወጣቱ እንዳለው የፈጠራ ስራው በመቀሌና በውቅሮ ከተሞች ተሞኩሮ ውጤታማነቱ መረጋገጡንና አንደኛ ደረጃ ተብሎ የምስክር ወረቀትና የ70 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቶታል፡፡ በተሰጠው የማበረታቻ ሽልማት መደሰቱንና ወደፊት ለላቀ የፈጠራ ስራ እንዲነሳሳ ብርታት እንደሰጠው ወጣት አሰፋ ገልጿል። የመስሪያ ቦታን ጨምሮ የሚደረግለት ድጋፍ ከቀጠለ ሌሎች የማንፋክቸሪንግ ኢንዳስትሪ ልማት ለማፋጠን የሚያግዙ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ማከናወን እንደሚፈልግም አመልክቷል፡፡ የጨርቃጨር ፋብሪካዎች የሚጠቀሙበትን የኬሚካል ቀለም በመፍጠር ጥቅም ላይ ያዋለ ሌላው  የፈጠራ ባለቤት ወጣት ሰሎሞን ተክለኃይማኖት ነው። በዚህ የፈጠራ ስራው ሁለተኛ በመውጣት የ65ሺህ ብር ተሸላሚ ለመሆን መብቃቱን ነው ወጣት ሰሎሞን የገለጸው። " ቀደም ሲል የፋብሪካ የኬሚካል ቀለም ከተለያዩ ሃገራት በውድ የውጭ ምንዛሬ ይገባ እንደነበርና አንዱን ኪሎግራም ሦስት የአሜሪካን ዶላር ያስወጣ ነበር "ብሏል። እሱ ወደ ሃገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርበው የኬሚካል ቀለም ግን አንዱን ኪሎ ግራም በ30 ብር ሂሳብ ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑን ተናግሯል። ወጣቱ ምርቱን ለዓድዋ አልመዳ፣ ኮምቦልቻ፣ ባህርዳርና ሌሎች የጨርቃጨር ፋብሪካዎች እያቀረበ መሆኑን ጠቅሷል። ሌላው ተሸላሚ ወጣት መኮንን ተክለማርያም  በበኩሉ በደቂቃ ከአስር በላይ እንጀራ እና ዳቦ የሚጋግር ማሽን ሰርቶ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፤ለመከላከያ ሰራዊትና  ሆስፒታሎች በማቅረብ ላይ መሆኑን ተናግሯል፡፡ አንዱን ማሽን በ30 ሺህ ብር በማቅረብ በአምሰተኛ ደረጃ የ50ሺህ ብር ተሸላሚ መሆኑ ያመለከተው ወጣት መኮንን እሱ የፈጠረው ማሽን ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ውጤታማ መሆኑን ገልጿል። የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንዳሉት በሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምርና የፈጠራ ስራዎች  ሰርተው ለሚያሰሩ ወጣት ምሁራን የክልሉ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው። "በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤት የታገዘ ስራና ልማት በሀገርና በክልል የተጀመረው እድገት ይበልጥ ለማፋጠን ወሳኝ ሚና አለው" ብለዋል፡፡ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ። ወጣቶቹ የጀመሯዋቸው የፈጠራ ስራዎች በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውሉ በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የበኩላቸውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም