ወጣቱ ለሀገር አንድነትና ሰላም በጋራ እንዲቆም የጋሞ አባቶች ጠየቁ

116
ወጣት ትውልድ ጥንት አባቶች ኢትዮጵያን ከወራሪ ጠላት መታደግ የቻሉበትን ፈለግ በመከተል ለሀገር አንድነትና ሰላም በጋራ እንዲቆም የጋሞ አባቶች ጠየቁ። የጥምቀት በዓልን  በጎንደር ከተማ ያከበሩት የጋሞ አባቶች በባህር ዳር ደግሞ  "ጀግና ይሰራል እንጅ አይወለድም" በሚል  መሪ ሃሳብ  ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት የጋሞ አባቶች ቡድን መሪ  አቶ  ካዎ ታደሰ ዘውዱ እንዳሉት ኢትዮጵያዊያን የውጭ ወራሪዎችን በጀግንነት ተጋድሎ በማሸነፍ የሀገራቸውን ሉአላዊነት አስከብረዋል። ይህም ዛሬ ኢትዮጵያዊያን በየትኛውም ዓለም አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱ ያስቻለ አኩሪ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ የሚስተዋለው የሰላም መታጣት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እርስ በእርስ በመፈቃቀር፣ በመመካከርና በመደጋገፍ መስራት እንደሚገባ መክረዋል። "የጋሞ አባቶች ከአርባ ምንጭ ተነስተን እስከ ጎንደር ያደረግነው ጉዞ ዓላማም በየደረስንበት ፍቅርንና መደጋገፍን በመስበክ ወጣቱ ትውልድ በአንድነት በመቆም የሀገሩን አንድነት እንዲያስጠብቅ  ለማስተማር ነው" ብለዋል። የአቶ  ካዎ ንግግር መግቢያ 0፡ 51" ጀግኖች አሉ...ለኔ ጀግና ነው" መውጫ 01፡47 "በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተሳስቦና ተፋቅሮ ከመኖር  ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም" ያሉት ደግሞ  ሌላው የቡድኑ አባል አቶ  አብረሃም አኔቦ ናቸው። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ጀግና  ሰላምን፣ አብሮነትን እና መቻቻልን አብዝቶ የሚሰብክ መሆኑን በመገንዘብ የጋሞ አባቶች ይህን ለመተግበር የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ወጣቱ ትውልድም የአባቶቹን  አደራ በመቀበል ከጥላቻ፣ ከግለኝነትና ከጽንፈኝነት አስተሳሰብ እራሱን በማራቅ ለሀገር አንድነትና ሰላም በጋራ እንዲቆም ጠይቀዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር መሃሪ ታደሰ በበኩላቸው አሁን የሚያስፈልገው የጀግንነት ተጋድሎ ሰላምን በማስፈ  ልማትን ለማፋጠን መረባረብ እንደሆነ ተናግረዋል። "ሰላምና ልማት ለማጋገጥም በህዝቦች መካከል የሚስተዋሉ ልዩነቶችን በውይይትና ድርድር በመፍታት የጋራ ተሳትፎንና ተጠቃሚነትን በማጎልበት ላይ መዝመት ነው "ብዋል። ሰላምን በህዝቦች መካከል ማስፈን በኩል የጋሞ አባቶች በተግባር እያሳዩት ያለው አኩሪ ተግባር በሀገር ደረጃ አርአያነት ያለው በመሆኑ  የአማራ ክልል ወጣቶች ፈለጋቸውን መከተል እንዳለባቸውም አሳስበዋል። የከተማ አስተዳደሩም በሰላምና  በተለያዩ የልማት ስራዎች ውስጥ ወጣቶችን  ቅድሚያ ሰጥቶ በማሳተፍ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋጋጥ የድርሻውን እንደሚወጣም አስታውቀዋል። በውይይት መድረኩ  የጋሞ አባቶች ፣ ከባህርዳር ከተማ የተወጣጡ ወጣቶች፣ ሴቶችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም