የአዲስ አበባ ምክር ቤት 7ኛ አመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ

159

አዲስ አበባ ጥር 15/2012 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ምክር ቤት 7ኛ አመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ

ጉባኤው በዛሬው ውሎው የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ ለማቋቋም፣ የከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለማሻሻል የወጡ አዋጆችን እንዲሁም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ረቂቅ ደንቦችን ጨምሮ ሌሎች ደንብና አዋጆችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል።

ከሰአት በኋላ በሚኖረው ውሎ ደግሞ የተለያዩ ሹመቶችንም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።