በጎ አድራጊው 10 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ቅርሶችና መጻህፍትን ለማህበሩ ለገሱ

109
ሽሬ እንዳስላሴ፤ ጥር 14 / 2012  (ኢዜአ) አንድ በጎ አድራጊ ግለሰብ በሕይወት ዘመናቸው የሰበሰቧቸውን 10 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ቅርሶችና መጻሀፍት ዛሬ ለሽሬ ልማት ማህበር አስረከቡ፡፡ ለማህበሩ የተበረከቱ ጥንታዊ፣ታሪካዊ ቅርሶችና መጻህፍት በዶክተር ሀብተማርያም አሰፋ የተሰባሰቡ ናቸው ። ‘’ቢሪንግተን ሆራይዘን አሰፋ’’ በተባሉ ጀርመናዊት ባለቤታቸው በኩል ከተለገሱት ቅርሶች መካከልም በወርቅና በብር የተሰሩ መስቀሎችና ጌጣጌጦች ይገኙባቸዋል። እንዲሁም በወርቅና በብር የተሰሩ የፈረስ ጌጣጌጦች፣የጥንታዊ የጦር መሠሪያዎች፣ባህላዊ የምግብ ማብሰያና ማቅረቢያ ቁሳቁስ ተካተውባቸዋል። ጥንታዊ ቅርሶቹና መጻሃፍቱ በ50 ዓመት የትዳር ቆይታቸው የተሰበሰቡ መሆናቸውን የበጎ አድራጊው ባለቤት ገልፀዋል። በሽሬ ልማት ማህበር በተገነባው ዲጂታል ቤተ መጻህፍት ውስጥ በዶክተር ሃብተማርያም አሰፋ ስም            ቤተ-መዘክር በመክፈት ለህዝብ እይታ እንደውል ይደረጋል ያሉት ደግሞ የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረኪዳን በርኽ ናቸው። የቅርሶቹ ርክክብ የተፈፀመው የአገር ሽማግሌዎችና በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሽሬ ካምፓስ ምሁራን በተገኙበት ነው። የቅርሶቹና የመጻህፍቱ አሰባሳቢ ዶክተር ሀብተማርያም አሰፋ በተያዘው ዓመት በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ እውቅ ደራሲና የቅርስ ተመራማሪ ምሁር ነበሩ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም