ጃፓን በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ለሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

97
ጥር፤ 14/2012 (ኢዜአ) ጃፓን በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ለሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። የኢትዮጵያና ጃፓን ግንኙነት ከ65 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን በነዚህ ጊዜያት የጃፓን መንግስት በኢትዮጵያ የሚከናወኑ በርካታ ፕሮጀክቶችን ሲደግፍ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ለሚገኝ ሻምቡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ማከናወኛ ስምምነት ተደርጓል። ለዚህም የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት የጃፓን መንግስት የ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ነው የተናገሩት። በዚህም ስምንት የመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት የታቀደ ሲሆን ፕሮጀክቱን በሰባት ወራት  ውስጥ ለማጠናቀቅም ታስቧል። ጃፓን በቀጣይም በኢትዮጵያ የሚከናወኑ ሌሎች ፕሮጀክቶችንም የምትደግፍ መሆኗን ተናግረዋል። የዞኑ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኜ አሰፋ እንደተናገሩት በትምህርት ቤቱ የሚገኙ የመማሪያ ክፍሎች የፈራረሱና ለመማሪያም ምቹ ያልሆኑ ናቸው። በዚህም በትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ 2ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን በአንድ ክፍል ውስጥም ከ60 እስከ 80 ተማሪዎች ታጭቀው የሚማሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የጀፓን ኤምባሲ ችግሩን ለመፍታትና ለተማሪዎች ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመፍጠር ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል። ይህም በተለይ የትምህርት ጥራቱን ከማሻሻልና ለተማሪዎቹም ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። ጃፓን እስካሁን በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከ400 በላይ የትምህርት፣ ጤና፣ ውሃ፣ ግብርና፣ የኮንስትራክሽንና ሌሎችም የልማት ፕሮጀክቶችን አከናውናለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም