የአዲስ አበባ ምክር ቤት ነገ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ይጀምራል

86
አዲስ አበባ ጥር 14/2012 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከነገ ጥር 15-17 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያካሄድ አስታወቀ። ጉባዔው ከከተማ አስተዳደሩ የተመረጡ ሁለት ቢሮዎችና ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ይወያያል። የተለያዩ አዋጆችና ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚቀርቡና ውይይት ተደርጎባቸው እንደሚጸድቁም ይጠበቃል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም