ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በዳቮስ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢኮኖሚ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

61
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 14/2012  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በዳቮስ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሱልጣን ቢን ሰይድ አል ማንሱሪ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ ትስስርና ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ በሚያድግበት አቅጣጫ ላይ ያተኮረ ነበር። የአገራቱ የኢኮኖሚ ትብብር ካላቸው ታሪካዊ ግንኙነት ባሻገር የሁለቱ አህጉር ቀጣናዊ ትስስር ማሳያ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ገልጸዋል። በሁሉም ዘርፎች ቀጣናው በሚጠይቀው የንግድ መስተጋብር ከፍታ የሀገራቱን ህብረ~ዘርፋዊ የኢኮኖሚ ትስስር ኢትዮጵያ በተሻለ አግባብ አጥብቃ እንደምትቀጥልም ተናግረዋል። የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሱልጣን ቢን ሰይድ አል ማንሱሪ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል እያደገ የመጣው  የኢኮኖሚ ትስስር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምቹ  ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም