ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከደቡብ ክልል ከተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጋር እየተወያዩ ነው

52
አዲስ አበባ ጥር 14/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከደቡብ ክልል ከተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጋር እየተወያዩ ነው። በውይይቱ ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የተወጣጡ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች ተገኝተዋል። የውይይቱ ዋነኛ ዓላማም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የክልልነት ጥያቄ በሚል መነሻ በክልሉ የሚፈጠሩ ያልተገቡ እንቅስቃሴዎችን በውይይት ለመፍታት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም በክልሉ በቀጣይ ሊፈጠሩ ለሚችሉ ችግሮች በጋራ መፍትሄ ማበጀትም ሌላው የውይይቱ አጀንዳ ነው። ይህን እውን ለማድረግም በዛሬው ውይይት ማጠናቀቂያ ላይ የጋራ ኮሚቴ ይዋቀራል ተብሎ ይጠበቃል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም