በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በደረሰ የጀልባ መስመጥ በትንሹ 15 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ - ኢዜአ አማርኛ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በደረሰ የጀልባ መስመጥ በትንሹ 15 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 13/2012 በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምዕራባዊ ክፍል በምትገኝ ሀይቅ ላይ በደረሰ የጀልባ መስመጥ በትንሹ 15 ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢውን አስተዳደር ዋቢ በመጥቀስ ቢቢሲ ዘግቧል። የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ እስካሁን እንዳልተቻለም ዘገባው አክሏል። እንደዘገባው ጀልባዋ ከቀብር ሥነ-ስርዓት የሚመለሱ ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎችን ጭና ስትጓዝ አዳጋው አጋጥሟታል። እ.ኤ.አ. በግንቦት ወር 2019 ከ400 በላይ ሰዎችን የጫነች ጀልባ ከሰመጠች በኋላ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የደረሰ አደጋ እንደሆነ በዘገባው ተመላክቷል። በጀልባዋ ላይ ተሳፍረው የነበሩት አብዛኞቹ የወር ደመወዛቸውን ለመቀብል የሄዱ መምራኖች እንደሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጀልባዎች ከመጠን በላይ በመጫን እና ደካማ የሆነ የጥገና በመኖሩ የተነሳ ተደጋጋሚ አደጋዎች እያስተናገዱ እንደሆነ ተጠቅሷል።