ቡርኪና ፋሶ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አወጀች

68

ጥር 13/2012 በሰሜናዊ ቡርኪና ፋሶ በደረሰው የሽብር ጥቃት 36 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት  ሮች ማርክ ክርስትያን የሁለት ቀን ብሔራዊ ሐዘን አውጀዋል፡፡

አሸባሪ ቡድን በሳንማቴንጋ ግዛት የሚገኘው ናግራጎ በተባለው የገበያ ማዕከል ላይ ባደረሰው ጥቃት 32 የተገደሉ ሲሆን በሌሎች ሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን እና ገበያው በእሳት መጋየቱን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ አላሙ በተባለው መንደር አራት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን የሀገሪቱ ምክር ቤት  ሲቪል ዜጎች በበጎ ፈቃደኝነት  በአገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ እስላማዊ ታጣቂዎች ጋር በሚደረገው ውጊያ እንዲካፈሉ የሚያስችል ሕግ አጽድቋል፡፡

በአሸባሪ ቡድኖች ተከታታይ ጥቃቶችን እያስተናገደች የምትገኝ  ቡርኪና ፋሶ እ.አ.አ     ከ 2018 ጀምሮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች፡፡

/ቢቢሲ /

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም