ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የስድስት ወራት ሥራዎችን ነገ ይገመግማል

57
(ኢዜአ) ጥር 13/ 2012 የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል። በስብሰባውም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትን እንደሚገመግም ተነግሯል።
በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ እንደሚያፀድቅም ተነግሯል። የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሴቶች ፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳባቸውን ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ። (ምክር ቤትጽ/ቤት)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም