በጮራ ወረዳ ተሽከርካሪ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ

148
መቱ ጥር 12/  2012 (ኢዜአ) በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ዛሬ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤አምስት ደግሞ መቁሰላቸውን ፖሊስ ገለጸ። የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የአካባቢ ፀጥታ ማረጋገጥ ሥራ ሂደት መሪ ሳጅን ዋቅጋሪ ጋዲሳ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው እኩለ ቀን ላይ ልዩ ስሙ ሀዋ የምበር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው። አደጋው የደረሰው ከያዮ ወረዳ ወደ ጮራ ወረዳ ሲጓዝ የነበረ የሠሌዳ ቁጥሩ ኦሮ 3-522558 የሆነ አነስተኛ የሕዝብ ተሽከርካሪ ከባጃጅ ታክሲ ጋር በመጋጨቱ ነው ብለዋል። በአደጋው የባጃጁን አሽከሪካሪ ጨምሮ በውስጡ የነበሩ አራት ሰዎች ህይወት ወዲያው ማለፉን ሳጅን ዋጋሪ ገልፀዋል። በሌላኛው ተሽከርካሪ የነበረ አንድ ግለሰብ ሕይወትም በአደጋው አልፏል። በአደጋ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው አምስት ሰዎች በደሌ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል። ፖሊስ የአደጋውን መንስዔ እያጣራ መሆኑን ሳጅን ዋጋሪ አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም