ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

438

ኢዜአ፤ ጥር 12/2012 በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ባተኮረው ውይይት የኢትዮጵያ እና የእንግሊዝ ግንኙታቸውን ወደ ላቀ የትብብር ከፍታ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በቤኪንግሃም ቤተመንግስት በተደረገው የእራት ግብዣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከልዑል ዊልያም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ልዑል ዊልያም ኢትዮጵያን የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው የገለፁላቸው ሲሆን፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ልዑሉ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ግብዣ አቅርበውላቸዋል።
(ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)