የጥምቀት በዓል አንድነትንና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ መከበር አለበተ-አቡነ ሩፋኤል

46
ጋምቤላ ጥር 11 / 2012 ምዕመናን የጥምቀት በዓልን አንድነትንና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲያከብሩት  በጋምቤላ  አንድ የሃይማኖት አባት  አሳሰቡ። በዓሉ በጋምቤላና ሌሎች የክልሉ ከተሞች በድምቀት እየተከበረ ነው። የጋምቤላ፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ፣የምዕራብ ወለጋና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሩፋኤል  እንዳስገነዘቡት በዓሉን ጥላቻንና ጽንፈኝነትን ባስወገደ መልኩ ማክበር ያስፈልጋል። የዘር፣ የቋንቋና የአካባቢያዊ ልዩነቶችን በማስቀረትም የጋራ እሴቶችን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ  አቡነ ሩፋኤል ገልጸዋል። የበዓሉ ታዳሚዎች በበኩላቸው በዓሉን በፍቅርና በአንድነት በድምቀት እያከበሩት እንደሚገኙ ገልጸዋል። በጋምቤላና በሌሎች የክልሉ ከተሞች በትናንትናው ዕለት የከተራ በዓልም በሰላም ተከብሯል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም