ጥምቀት የአብሮነት ተምሳሌትና የሰላም በዓል ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ያስፈልጋል-አቡነ ህርያቆስ

120

ሆሳዕና ጥር 10 /  2012  (ኢዜአ) የጥምቀት በዓል የአብሮነት ተምሳሌትና የሰላም በዓል ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቡነ ህርያቆስ አሳሰቡ።

የጥምቀት በዓል የአብሮነት ተምሳሌትና  የሰላም በዓል ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቡነ ህርያቆስ አሳሰቡ።

የከተራ በዓል በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው።

በሀድያ፣ ከምባታ፣ ስልጤ፣ ሰሜንና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጻጻስ ብፁህ አቡነ ህርያቆስ ለኢዜአ እንዳስረዱት በዓሉ የአንድነትና የፍቅር ብሎም የሰላም ሆኖ ለትውልድ እንዲሸጋገር መስራት ይገባል።

በዓሉ ኢትዮጵያውያን በአብሮነት በሰላምና በመከባበር የምናከብረው በመሆኑም አኩሪና በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ በዓል ሆኗል ብለዋል፡፡

ምዕመናን ከአምላክ የተሰጠውን ሰላምን በማስጠበቅና አብሮነትን በማስቀጠል ድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አቡነ ህርያቆስ አስገንዝበዋል፡፡

ምዕመናን ከመንግሥት ጎን በመሆን ለአገር ሰላምና ልማት መስራት አለባቸው በማለት ምክራቸውን ለግሰዋል።

በኢትዮጵያ የዘንድሮው መስቀል በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ)ከተመዘገበ ወዲህ ነገ ለመጀመሪያ ጊዜ ይከበራል።