በሆሳእና የከተራ በዓል እየተከበረ ነው

67
ሆሳእና፤ ጥር 10 / 2012 (ኢዜአ)  በሐዲያ ዞን በሆሳእና ከተማ የከተራ በዓል መከበር መጀመሩን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት አስታወቀ። በነገው ዕለትም የጥምቀት በዓል እንደሚከበርም ገልጿል። የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ቢንያም መንቸሮ ለኢዜአ እንደገለጹት ቤተክርስቲያኗ በከተማው ለጥምቀትና ደመራ በዓል ማክበሪያ ቦታ እንዲሰጣት ለሀዲያ ዞን አስተዳደር ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል። ቤተ ክርስቲያኗ ዛሬ የከተራ በዓል እያከበረች መሆኗንም አስታውቀዋል። ነገም የጥምቀት በዓልን ለማክበር ዝግጅት  እያደረገች መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም