አየር መንገዱ በጥቃቱ ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባችው ወገኖች ሃዘኑን ገለጸ

63
አዲስ አበባ ሰኔ 17/2010 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሃዘኑን ገለጸ። በአገሪቱ የተጀመሩ አዳዲስ ለውጦችን ስኬታማ ለማድረግ ከህዝብ ጋር በመሆን መንግስትን እንደሚደግፉ የአየር መንገዱ ሰራተኞች መግለጻቸውን ባወጣው መግለጫ አስውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን በመመኘት በሃዘናቸው ከጎናቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ ወዲህ ለጀመሯቸው ለውጦች ምስጋና ለማቅረብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በነበረው የድጋፍ ሰልፍ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት እስካሁን የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ ከ150 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም