በዱግዳ ወረዳ ትናንት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 27 መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ

168

ኢዜአ ታህሳስ 20/2012 በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ትናንት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 27 መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ ለኢዜአ እንደገለፁት ትናንት ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ከዝዋይ ወደ መቂ በመጓዝ ላይ የነበረ ሚኒባስ በተቃራኒው አቅጣጫ ከሚመጣ  የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር በመጋጨታቸው የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉን ኢዜአ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ሚኒባሱ 14 ሰዎችን ማሳፈር ሲገባው በወቅቱ 27 ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ እያለ ነበር አደጋው የደረሰበት፡፡

በዚሁ አደጋ ሾፌሩን ጨምሮ በሚኒባሱ ውስጥ የተሳፈሩት ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው አንድ እናት ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ህይወታቸው ማለፉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የአውቶብሱ አሽከርካሪ ለፖሊስ እጁን መስጠቱን የገለፁት ኮማንደር አስቻለው የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም