መገናኛ ብዙሃን በግለሰቦችና በቡድኖች ነጻነታቸውን እያጡ መጥተዋል ተባለ

627

ኢዜአ  ታህሳስ 15/2012.. መገናኛ ብዙሃን ከዚህ ቀደም በመንግስት ይደርስባቸው ከነበረው ነጻነት የማጣት ችግር ባለፈ በአሁኑ ወቅት በግለሰቦችና በቡድኖች አማካኝነት ነጻነታቸውን እያጡ መሆኑ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የህዝብና የግል መገናኛ ብዙሃን በግለሰቦችና በቡድኖች በሚደርስባቸው ጫና የሙያ ነጻነታቸውን እያጡ መሆኑ ተገልጿል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በየወሩ የሚካሄደው የአዲስ ወግ የውይይት መድረክ ‘የሚዲያ ሚና አሳቦችን ለማቀራረብ’ በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የግል መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች፣ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ባለሙያች፣ ታወቂ ግለሰቦች፣ ፖለቲከኞች እና ሌሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ ‘ሚዲያ በሽግግር ወቅት’ በሚል ርዕስ የመወያያ መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በዚህም ጊዜ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ሚና እንደ ነባራዊ ሁኔታ የሚለያይ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይ የጸር ሽብር አዋጅ መጽደቅ በአገሪቱ የሚዲያ ታሪክ አሉታዊ አስተዋዕጾ እንደነበረው አስታውሰዋል።

በአሁን ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ከባለፉት ዓመታት የተሻለ ቢሆንም ከመንግስት ባለፈ ከግልሰቦችና ከቡድኖች በሚደርስ ጫና የሙያ ነጻነት እየቀጨጨ መምጣቱን ዶክተር ሙላቱ ተናግረዋል።