ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር  ተወያዩ

861

ኢዜአ፤ ታህሳስ 6/2012 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ዛሬ በጄኔቫ ተወያይተዋል፡፡

ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በሁሉአቀፍ የጤና ሽፋን፤ በቅድመ ጤና አጠባበቅ፤ በተመጣጠነ ምግብ፤ በፋማሲዮቲካል አቅርቦት እና በአቅም ግንባታ ዙሪያ ጄኔቫ በሚገኘው የድርጅቱ ፅ/ቤት በስፋት መክረዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ልማት የሚጫወተውን አጋዥ ሚና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ አድንቀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው፤ የዓለም ጤና ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት እንደሚያጠናክር ገልፀው፤ በውይይቱ በተነሱ ነጥቦች ዙሪያ የድርጅቱ ድጋፍ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።