ናይጄሪያ አፍሪካውያን የመዳረሻ ቪዛ መስጠት ልትጀምር ነው

54

ኢዜአ፤ ታህሳስ 2/2012 የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ ወደ ሀገሪቱ ለሚጓዙ ሁሉም አፍሪካውያን በመጪው ጥር ወር የመዳረሻ ቪዛ መስጠት እንደሚጀመር ገልጸዋል።

የመዳረሻ ቪዛው ተጓዦች ከዚህ ቀደም ወደ ናይጄሪያ ለመሄድ የሚያስችል ቪዛ ለማግኘት በኤምባሲዎች በኩል ማመልከት ይጠበቅባቸው የነበረውን ሂደት ያስቀራል ነው የተባለው።

ፕሬዚዳንቱ ናይጄሪያ “አፍሪካውያን በአፍሪካ በነጻ እንዲንቀሳቀሱ” ቁርጠኝነቷን እያሳየች መሆኑን ተናግረዋል።

ቡሃሪ ይህን ቢሉም እርሳቸው ለፓን አፍሪካ የአንድነት እንቅስቃሴ የሚሰጡት ቦታ ዝቅተኛ ነው በሚል ይተቻሉ።

ከነሐሴ ወር ጀምሮ ናይጄሪያ ከጎረቤቶቿ ጋር የምትዋሰንባቸውን ድንበሮች ሙሉ ለሙሉ በመዝጋት የድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጥና የሰዎች እንቅስቃሴን መግታታቸውም ተነግሯል።

ቡሃሪ አዋሳኝ መስመሮችን እንዲያስከፍቱ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ያሉ ሲሆን፥ የድንበሮቹ መዘጋት ዓላማ ወደ ናይጄሪያ የሚገቡ ምርቶችን ለመከልከልና ሀገሪቱ በምግብ ምርት ራሷን እንድትችል ለማድረግ ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም