በኒጀር ጦር ሰራዊት ካምፕ በተፈፀመ ጥቃት 73 ወታደሮች ተገደሉ

111

ኢዜአ፤ታህሳስ 2/2012 በምዕራብ ኒጀር ጦር ካምፕ ላይ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ 73 ወታደሮች መገደላቸውን የሀገሪቱ ጦር ሰራዊት ገልጿል ፡፡

ሌሎች አሥራ ሁለት የሚደርሱ ወታደሮች ደግሞ በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

የኒጀር የመከላከያ ሚኒስትር ኢሱፉቱ ካታምቤ ጥቃቱን በተመለከተ እስካሁን ድረስ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል አለመኖሩን ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ከግድያው ጀርባ ያለው መሰረቱን በናይጄሪያ  ያደረገው ቦኮ ሃራም ሳይሆን እንደማይቀርም  ገልፀዋል ፡፡

በማሊ ድንበር አቅራቢያ  ኢናትስ አካባቢ  ከባድ ጦርነት እንደነበረ ሚንስትሩ  ተናግረዋል ፡፡

ጥቃቱ የተፈፀመው አምስት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ከፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮን ጋር  በፀጥታ ጉዳይ  ከተወያዩ ከአንድ ቀን በኋላ ነው፡፡

የኒጀር መንግሥት ከሁለት ዓመት በፊት ታውጆ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  ለሦስት ወራት ለማራዘም ጥያቄ አቅርቧል ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም የሀገሪቱ ጦር ታጠቂ ቡድኖችን ለመደምሰስ እየሰሩ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም