ሩዋንዳ የኢቦላ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች

155

ኢዜአ፤ ህዳር 29/2012 ሩዋንዳ የኢቦላ በሽታን የሚገታ  የክትባት ዘመቻን  ለመጀመሪያ ግዜ መስጠት ጀመረች።

የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዘመቻው ክትባቱ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚዋሰኑ  ቦታዎች  ለ200 ሺ ሰዎች  ይሰጣል ብለዋል፡፡

የጤና ሰራተኞች፣ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ፣ ፖሊሶች እና ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ላይ ለተሰማሩት  የህብረተሰብ  ክፍሎች ክትባቱ በቅድሚያ  ይሰጣችዋል ተብሏል፡፡

በሩዋንዳ እስከ አሁን ምንም ዓይነት የኢቦላ በሽታ አለመታየቱ ቢገለጽም፤ በጎረቤት  ሀገር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ በሽታ ምክንያት ከባለፈው ነሃሴ ጀምሮ ከ2 ሺ 200 ሰዎች በላይ መሞታቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክንያትም ክትባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ  በምትገኘው  ጎማ  ሲሆን፤ እስከ አሁን ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ ኮንጎውያን ክትባቱ  እንደተሠጣቸው  የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም