ምስጉን አሽከርካሪዎች ተሸለሙ

107
ኢዜአ ህዳር 27/2012 ላለፉት አምስት ዓመታት በሙያቸው ምስጉን ለሆኑ አሽከርካሪዎች የሜዳልያ ሸልማት ተበረከተላቸው። 'እንደርሳለን' የተሰኘ በትራፊክ አደጋ ላይ ያጠነጠነ አገር አቀፍ የማህበረሰብ ንቅናቄ መድረክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ተካሂዷል። በዚህ መድረክ ዕውቅና ያገኙት አሽከርካሪዎች ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተለዩ ሲሆን በተቀመጡ መስፈርቶች ከ90 በመቶ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው። በጠንቃቃነት የተለዩት  51   አሽከርካሪዎች  ሽልማትና ዕውቅናውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እጅ ተቀብለዋል። በተጨማሪም የትራፊክ አደጋ ለደረሰባቸው ተጎጂዎች አገልግሎት በመስጠት ግለሰቦችና ተቋማትም ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል። ከተሸላሚዎቹ መካከል የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ክፍል እና የክፍሉ ባልደረባ ዶክተር ብሩክ ላምቢሶ፤ ከኢትዮጵያ አጥንት ህክምና ማህበር ዶክተር ገለታ ተሰማ፣ የትራፊክ ፖሊስ ባልደረባ ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ እና ብርሃን ባንክ ይገኙበታል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም