የአዴፓ አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ዙሪያ እየተወያዩ ነው

159

ህዳር 26/2012 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ የክልል አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ዙሪያ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ መወያየት ጀምረዋል።

አመራሮቹ ትላንት የብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ በንባብ ቀርቦ በቡድን የተወያዩ ሲሆን የተነሱ የግልጽነት ጥያቄዎች ላይ ዛሬ በጋራ መድረክ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ አቶ ላቃቸው አያሌውና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተወያዩ ይገኛሉ።

በመድረኩ ላይ ከወረዳ ከዞንና ከክልል የተወጣጡ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን በቀጣይም በተዋረድ እስከታችኛው የአመራር እርከን ድረስ ውይይቱ እንደሚቀጥል ታውቋል።