በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና መሰረታዊ እሳቤ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

81
ኢዜአ ህዳር 26/ 2012 በፌዴራል ደረጃ የኢህአዴግና የአጋር ፖለቲካ ድርጅቶች አመራር አባላት በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና መሰረታዊ እሳቤ ላይ እየተወያዩ ነው። ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) አባል እና አጋር ድርጅቶች ብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል በጉባዔያቸው ውሳኔ ማሳለፋቸው ይታወሳል። በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲ ስምንቱ ፓርቲዎች የተቀላቀሉት ሲሆን፤ ይህንኑ ሊቀ መናብርቱ በፊርማቸው ማጽደቃቸው ይታወሳል። ዛሬ እየተካሄደ ባለው መድረክ የኢህአዴግ መልካም ድሎች፣ አደረጃጀትና የውህደት አስፈላጊነት የሚያሳይ ውይይት መነሻ ሃሳብ ቀርቧል። መነሻ ጽሁፉን ያቀረቡት በኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪከ ማኅበራት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አለሙ ስሜ ናቸው።   ባለፈው ሳምንት ስምንቱ ፓርቲዎች በፊርማቸው ውህደቱን ሲያጸድቁ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የሚያሸጋግር ድልድይ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም