በቡሩንዲ በመሬት መንሸራተት በትንሹ 24 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

100

ኢዜአ፤ ህዳር 26/2012 በምዕራብ ቡሩንዲ ባቢቶኬክ ግዛት  ውስጥ በምትገኘው ሙጊና ወረዳ የጣለው ከባድ ዝናብ  ባስከተለው  የመሬት መንሸራተት  በትንሹ  24 ሰዎች እንደሞቱ ቢቢሲ ዘገበ፡፡

የቡሩንዲ የደህንነት ሚኒስትር ቃል አቀባይ ፒየር ኒኩሪኪዬ  በመሬት መንሸራትቱ ምክንያት ቤቶቹ ከተደረመሱ በኋላ የህይወት አድን ተግባራት መቀጠላቸውን ተናግረዋል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በአካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት በማስከተሉ ቤቶችን በማፈራረስ አፈር ውስጥ እንደቀበራቸው ተጠቅሷል።

በመረት ውስጥ የተቀበረውን አስከሬን የማውጣት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ማንነት እንዳይገለፅ የፈለገ ባለሥልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል   መናገሩን ዌብ በማድረገ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከባድ ዝናብ በኮሮብታማ አከባቢዎች በሚዘንብበት ወቅት የመሬት መንሸራትት እንደሚያስከትል የቡሩንዲ ኤስ ኦ ኤስ  መረጃው አትቷል።

በምስራቅ አፍሪካ የጣለው ያልተጠበቀ ከባድ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ በማስከተሉ በኬንያ እና ኡጋንዳ በትንሹ የ130 ሰዎችን ህይወት እንደቀጠፈ ቢቢሲ በዘገባው አውስቷል።

ፓዋን ተብሎ የሚጠራው  አውሎ ነፋስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደ ሶማሊያ የባህር ዳርቻ እየተቃረበ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡