ለዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች የሰላም ጥሪ ቀረበ

66

ኢዜአ ህዳር 25 /2012 ዓ.ም  የአማራና የኦሮሞ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ለዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ። የሃይማኖት አባቶች ፣የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ባደረጉት የሰላም ጥሪ አሁንም በከፍተኛ የትምህረት ተቋማት ትምህርታቸውን ያልጀመሩ ተማሪዎች እንዳሉ ገልጸዋል።

እነዚህ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ገብተው ሰላማዊ የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲቀጥሉ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎቹ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በተለይ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ዩኒቨርስቲዎች ወደትምህርት ገበታቸው የተመለሱ መሆኑን የጠቀሱት የሃገር ሽማግሌዎቹ ሌሎቹም ይህንን ጥሪ ተከትለው ወደሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

አንዳንድ ግለሰቦችም ተማሪዎችን ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረጓቸው እንደሆነም ታውቋል፤እነዚህም ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሃይማኖት አባቶች አሳስበዋል።

በትምህርት ገበታቸው ያልተገኙ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ወደትክክለኛ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲገቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

መምህራንም የነገ የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆኑ ተማሪዎችን በአግባቡ በማረቅ ኃላፊነታቸውን ይወጡ ዘንድም አሳስበዋል።

የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች የተውጣው አብይ ኮሚቴዎች  ወደ መማር ማስተማሩ ያልገቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መምህራን፣ ተማሪ  እና የአካባቢ ነዋሪዎችን ያወያያሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም