በትግራይ ታሪካዊ ስፍራዎችና ቅርሶች ላይ አተኩሮ የተዘጋጀ መፅሃፍ ተመረቀ

104
ኢዜአ ህዳር 21/2012 በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈጥራዊና ሰው ሰራሽ የሆኑ ታሪካዊ ስፍራዎችና ቅርሶች ላይ አተኩሮ የተዘጋጀ መፅሃፍ ዛሬ ተመረቀ። "ጆኦ ቱሪዝም "በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀው መፅሃፍ  ፕሮፌሴር ጃንሶን ሻው በተባሉ   በቤልጄየምያዊ ምሁር ነው። መፅሀፉ ከሶስት መቶ በላይ ገፅ እንዳለውና ለማዘጋጀትም የታሪካዊ ስፍራዎች እምብርት የሆነው ማዕከላዊ ዞን ደጉአ ተምቤን ወረዳ ውስጥ ለ25 ዓመታት ያህል በመላለስ  ሲያጠኑ መቆየታቸው ፕሮፌሰሩ በምርቃው ስነሰርዓት ወቅት ገልጸዋል። በወረዳው የሚገኙ ከአለት የተፈለፈሉ አስገራሚ ዋሻዎች፣ ተራራዎች ፣ ገደማትና አብያተ ክርስትያናት አንዲሁም ብርቅየ የሆኑ የዱር አራዊቶች በመፅሃፉ ተካተውበታል። የደጉአ ተምቤን ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ተክላይ ተክለማርያም በበኩላቸው ፕሮፌሴር ጃንሶን ሻው   አካባቢውን  ታሪካዊ ስፍራዎችና ቅርሶች በዓለም ለማስተዋወቅ የሚያግዝ መፅህፉ በማዘጋጀታቸው በወረዳው ህዝብ ስም አመስግነዋል። ምሁሩ በተጨማሪም  በወረዳው የአየር ንብረት መዛባት መከላከል ሚችሉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ለማስፋፋት የሚያግዙ የሙያና የገንዝብ ድጋፍ ሲያደርጉ እንደቆዩም አመልክተዋል። " መጽሃፉ የክልላችን ተፈጥራዊና ሰው ሰራሽ ሃብታችን ለዓለም ማህበረሰብ የሚያሳይ መስታወት ነው" ያሉት ደግሞ  በወረዳው መምህርት የሆኑት  አሚት ብርሃን ናቸው። በኢትዮጵያና በውጭ ሀገራት ለሽያጭ ይቀርባል በተባለው በዚሁ መፅሃፉ ምረቃ ወቅት ምሁራን ፣  የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና   ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በየትግራይ ክልል  ለጉብኚዎች መስህብና የገቢ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ከ6ሺህ በላይ የተለያዩ  ቅርሶችና ስፍራዎች እንደሚኖሩ ተመልክቷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም