ኢትዮጵያ የዩኔስኮ የዓለም አቀፍ የቅርስ ኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች

90
ኢዜአ ህዳር 18 / 2012 ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስ ኮሚቴ አባል መሆኗ ተጠቆመ። ኢትዮጵያ በ 40ኛው የዓለም አቀፉ የሳይንስ ትምህርትና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጉባኤ ላይ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው  መሪነት ተሳትፋለች። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የ 120 አገራት  የባሀል ሚኒስትሮችም ተካፋይ ሆነዋል። በጉባዔው የተመረጠችው ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ወቅት የዩኔስኮ የስራ አስፈፃሚ ቦርድና የዓለም አቀፍ ቅርስ ኮሚቴ አባል ሆናም ታገለግላለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አገሪቷ አባል እንድትሆን ለመረጡ አገራት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቅርስ ኮሚቴ የ21 ሀገራት ተወካዮችን በውስጡ የያዘ ነው። ኮሚቴው ቅርሶች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርትና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መዝገብ ላይ እንዲሰፍሩና ቅርሶቹ አደጋ ላይ ሲወድቁም እንዲሰረዙ የማድረግ ሙሉ ስልጣን ያለው መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። ኢትዮጵያ ይህን አባልነቷን ባህልን ሰላምና ልማት ለማምጣት እየተጠቀመችበት መሆኑም ይታወቃል። በአገሪቷ ያሉትን ባህላዊ ሃብቶች ለስራ ፈጠራና ለዘርፉ ኢንቨስትመንት በማፍሰስ ኢንዱስትሪውን ለገቢ ማግኛ ለመጠቀም እየሰራች ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም