“የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት” በአህጉሪቷ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ይሰራል

107

ኢዜአ፤ ህዳር 18/2012  “የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት” በአህጉሪቷ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አሰታወቀ።

የቀጣዩን ዓመት የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት መድረክን ለማስጀመር ከየአገራቱ የተውጣጡ አስተናጋጆች፣ የፖለቲካ መሪዎች እና የግብርና ተመራማሪዎች በሩዋንዳዋ ዋና ከተማ ኪጋሊ መሰብሰባቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

መድረኩም በ21ኛው ክፍለ-ዘመን የአፍሪካን የግብርና ዘርፍ እያጋጠሙት ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የታሰበ የአስር ዓመት እቅድ የያዘ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

የረሃብ እና የምግብ ዋስትናን በማዕከል ደረጃ በሚመለከት ከኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ከቀጠናው ያለውን ትብብር ለማሳለጥ የሚያስቡ መሪዎች ሁሉ በመጪው መስከረም ወር ላይ በኪጋሊ በሚካሄደው የምግብ ምርት ዓለም አዲስ መድረክ ላይ ድምፃቸውን ያሰማሉ ተብሏል፡፡

መድረኩም ከ1960ዎቹ ጀምሮ በላቲን አሜሪካ እና ደቡብ ምሥራቅ እስያ በመላው ሃገራት  “የግብርና ዘርፍን የሚያጠቃልል የቴክኖሎጂ ሽግግር” የሚል ስያሜ የተሰጠው  እንደነበረም ዘገባው አስታውሷል፡፡

በሁነቱ ወቅትም የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ-ማሪያም ደሳለኝ እና የሩዋንዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢድዋርድ ነጊሬነቴ ጨምሮ በቃል-አቀባይ ደረጃ መገኘታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

መድረኩም በአለፉት አመታት በአህጉሪቱ የምግብ ስርዓትን ለማሳደግ ልዩ ልዩ ድጋፍ  ላደረጉ የፈጠራ ልማት እርሻ አምራች ባለሙያዎች የገንዘብ ሽልማት መስጠቱንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት 80 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ምግብ በአነስተኛ ኢንዱስትሪ የሚያመርቱ የአርሶ አደር ቤተሰቦች መኖራቸውን አዘጋጆቹ እንደነገሩት ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም