በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አርባምንጭ ከነማን 6 ለ 5 አሸነፈ

73
አርባምንጭ ሰኔ 14/2010 በ2ኛው ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከነማ በሜዳው ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ 6 ለ 5 በሆነ ውጤት ተሸነፈ ፡፡ ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገውን ጉዞ ለማሳመር በሁለቱም ክለቦች ጥሩ የማጥቃት እንቅስቃሴና የጎል ሙከራ ተደርጓል ፡፡ በ16ኛው ደቂቃ ሴነጋላዊው ባፕቲስት የበረኛውን ስህተት በመጠቀም ቀዳሚውን ጎል ለኢትዮጵያ ቡና ሲያስቆጥር  በ33ኛው ደቂቃ የአዞዎቹ ፍቃዱ መኮንን የአቻነትን ጎል ማስቆጠር ችሏል ፡፡ ሆኖም ግን ጨዋታው 1ለ1 በሆነ ውጤት ቢጠናቀቅም በመለያ ምት ኢትዮጵያ ቡና  ወደ አራት ቡድኖች ለመቀላቀል የሚያስችለውን 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል ፡፡ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ዲዲዬር ጎመዝ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት “ለሰባት ዓመታት የጥሎ ማለፍ ዋንጫ አግኝተን አናውቅም ነበር'' ብለዋል ፡፡ “ዛሬ ተጫዋቾቼ በርካታ የጎል ዕድሎችን ቢያመክኑም በመለያ ምት ማሸነፋችን ደስታችን ጣፋጭ አድርጎታል'' ነው ያሉት ፡፡ “በቀጣይ ከሃዋሳ ከነማ ጋር ያለውን ጨዋታ በድል ለመወጣት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለንም'' ብለዋል ፡፡ የአርባ ምንጭ ከነማ ምክትል አሠልጣኝ ማቴዎስ ለማ ስለጫዋታው ተጠይቀው አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም ፡፡        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም