የአፍሪካ ወጠቶች በሰላም ግንባታ በሚጫወቱት ሚና ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ስብሰባ በአዲስ አበባ ዛሬ ተጀመረ

1816

ኢዜአ ህዳር 16/2012 የአፍሪካ ገራት ወጠቶች በሰላም ግንባታ ሂደት በሚጫወቱት ሚና ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ስብሰባ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ተጀመረ።

“ወጣቶች ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ስብሰባ የሚካሄደው በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲሆን ከመላው የአፍሪካ አገራት የተጋበዙ ወጣቶች ታድመውታል።

የሰብሰባው ዋና ዓላማ በአፍሪካ የሚገኙ ወጣቶች ለሰላም የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ በማሳደግ በአህጉሪቱ የሚታዩ የሰላም መደፍረስ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት የሚቻልበትን መንገድ ማመላከት  ነው።

በስብሰባው በአገር ግንባታ የወጣቶች ድርሻና ተሳትፎ ለሰላምና ለአገር ግንባታ፣ የወጣቶች ሚናና የግጭት መንስኤና መፍትሄ ላይ የሚያተኩሩ ጥናታዊ  ጽሁፎች ይቀርባሉ።

በሰላም ግንባታ ሂደት የአገራት መልካም ተመክሮም ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር ኢስማኤል ቼርጌ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል።

ስብሰባውን በመተባበር ያዘጋጁት የሰላም ሚኒስትር፣ የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ናቸው።