የትግራይ ልማት ማህበር ከአንድ ሺህ የሚበልጡ የዳስ መመሪያ ክፍሎች ወደ ህንጻ ሊቀይር ነው

57
ኢዜአ ህዳር 13/2012 ትግራይ ልማት ማህበር ከአንድ ሺህ የሚበልጡ የዳስ መማሪያ ክፍሎች ወደ ህንጻ ለመቀየር ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር ዛሬ ተፈራረመ፡፡ የትግራይ  ልማት ማህበር ከአንድ ሺህ በላይ የዳስ መማሪያ ክፍሎች ወደ ህንጻ ለመቀየር ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ተፈራረመ፡፡ በፊርማው ስነሰርዓት ወቅት የማህበሩ  ቦርድ ሰብሰቢ ኢንጂነር ታደሰ የማነ በክልሉ ሶሰት ሺህ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ አንድ ሺህ የዳስ የመመሪያ ክፍሎች ወደ ህንጻ ለመቀየር መወሰናቸውን ገልጸዋል። ማህበሩ  ከዳስ ወደ ህንጻ ለመቀየር 300 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚጠይቅ አመልክተው ይህንንም  ከአባላት ፣ ከነጋዴዎች ከሌሎችም ድጋፍ ሰጪዎች በሚሰበሰበው ገንዘብ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል። ልማት ማህበሩ በሚያስገነባው መማሪያ ክፍሎች 50ሺህ ያህል ተማሪዎች በምቹ ሁኔታ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ያግዛል፡፡ የልማት ማህበሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ገብረእግዚአብሔር በዳስ ውስጥ የሚማሩ ህጸናት  ለነፋስ ፣ ለፀሐይ ብርድ የተጋለጡ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ መማሪያ ክፍሎቹ ከዳስ ወደ ህንጻ በመቀየር ተማሪዎችን ከችግር ለመታደግ ሁሉም ህብረተሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ የመማሪ ክፍሎቹ መሻሻል በተማሪዎች ላይ የሚታየው የማቋረጥና ክፍል የመድገም ችግር እንደሚያቃልለው የተናገሩት ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ባህታ ወልደሚካኤል ናቸው፡፡ ከማህበሩ ጋር የተፈራረሙት  በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ የሚገኙት የዳስ መማሪያ ክፍሎች በባለቤትነት ስለሚያስተዳድሯቸው  እንደሆነ  አመልክተዋል። የመቀሌ ከተማ ነዋሪ አቶ ጌታቸው ደስታ በሰጡት አስተያየት የመማሪያ ክፍሎቹ ምቹ መደረጋቸው ተማሪዎች እውቀት ጨብጠው  ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን ስለሚያግዝ  የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። መምህር ዓንዶም አብረሀ በበኩላቸው  ህፃናቱ  ተገቢውን እውቀት ገብይተው ለተሻለ ውጤት እንዲበቁ  ለማስቻል ማህበሩ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ሁሉም ሊደገፈው  እንደሚገባ አመልክተዋል። ማህበሩ ከተመሰረተ ከ30 ዓመታት በፊት ጀምሮ እስካሁን  በክልሉ ከ700 በላይ ትምህርት ቤቶች እና ከ80 በላይ የህክምና ተቋማት በማስገንባት ለአገልግሎት ማብቃቱ ተገልጿል፡፡ በትግራይ ክልል አንድ ሚሊዮን 600ሺህ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ እንደሚገኙ ከትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ይገልጻል፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም