ቦርዱ የሲዳማ የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ይፋ አደረገ

1408

ኢዜአ ህዳር 13/2012 ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ የክልልነት ህዝበ ውሳኔ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ይፋ አደረገ

ቦርዱ  ውጤቱን  ይፋ ባረገበተው ውቅት እንደገለጸው  ሲዳማ በክልልነት እንዲደራጅ ድምፅ ለመስጠት ከተመዘገበው አብዛኞው  መርጧል።

ድምፅ ለመስጠት ከተመዘገበው   ሀዝብ ውስጥ 2 ሚሊዮን 777ሺህ 063 ድምጽ መሰጠቱን ቦርዱ አስታውቋል።

ድምጽ ከሰጠው 2ሚሊዮን 225ሺህ 249 የሚሆነው ሻፌታን 33ሺህ 463 የሚሆነው ደግሞ ጎጆን መምረጡን ቦርዱ ይፋ አድርጓል

ወጋ አልባ የሆኑ የድምጽ መስጫ ወረቀቶችም እንደሉ ተመልክቷል።

በውጤቱም መሠረት የዞኑ ነዋሪዎች  በፈቃዳቸው በሰጡት ውሳኔ መሰረት ሲዳማ ክልል ሆኖ መደራጀት የሚያስችል ድምጽ ማግኘቱን  ቦርዱ አስታውቋል።