ኢዜማ ከምዕራብ ኦሞና ቤንች ሸኮ ዞን የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያየ

58
ኢዜአ ህዳር 13/2012 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ-ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከምዕራብ ኦሞና ቤንች ሸኮ ዞን የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ዛሬ በሚዛን አማን ከተማ ውይይት አካሂደ። የኢዜማ ፀሐፊ አቶ አበበ አካሉ በዚህ ወቅት "ፓርቲው ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ኢኮኖሚና ፖለቲካ ዘርፎች እኩል ተጠቃሚ የሚችሉበት ስርዓት እንዲመጣ ይሰራል “ብለዋል። በዜጎች መካከልም ልዩነትን የሚፈጥሩ አሰራሮችን እንደሚታገል ገልጸው ጠንካራ ሀገራዊ አንድነት እንዲፈጠር የፓርቲው ትኩረት መሆኑን ተናግረዋል። ውይይቱን ያዘጋጁት እራሳቸውን ለማስተዋወቅ  እንደሆነና ፓርቲው በሀገራዊ ምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ  ለመሆን በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል። በኢዜማ የቤንችሸኮ ምዕራብ ኦሞና ሸካአካባቢዎች ጽሀፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ደነቀ ደሳለኝ በዞኖቹ   ፓርቲያቸው በነፃነትእያስተዋውቁ  መሆናቸውን ገልጸዋል። ከውይይቱ ተሳታፊ ነዋሪዎች መካከል አቶ ፈድሉ ያሲን በሰጡት አስተያየት ሀገሪቱን ከችግር ለማውጣት  ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ተባብረው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። ዜጎች በሀገራቸው በነፃነት ተንቀሳቅሰው ሰርተው መለወጥ የሚችሉበት ስርዓት ላይ ማተኮሩ ተገቢ መሆኑንም ገልፀዋል። የፓርቲው ቀዳሚ ተግባር ዜጎች በሀገራቸው ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት እንዲያደረግ ፍላጎታቸው መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ ዘሪሁን አሰፋ ናቸው። በቀጣይ ጊዜያትም ጠንካራ አቅም ያለው ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲኖርም እንዲሁ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም