በተሽከርካሪ አደጋ ስድስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ህይወት ጠፋ

61
ህዳር 12/2012ዓ.ም በከንባታ ጠምባሮ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ወረዳ ዛሬ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የስድስት ሰዎችን ህይወት ማጥፋቱን ፖሊስ አስታወቀ። የዞኑ ፖሊስ አዛዥ  ኮማንደር ማቲዎስ አደጎ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው የየደረሰው ከማለዳው 12 ሰዓት አከባቢ በሀደሮ ጡንጦ ወረዳ በተለምዶ ሌሾ ማዞሪያ  ነው። የታርጋ ቁጥሩ  ኮድ 3-14854 አዲስ አበባ  ኤፍኤስ አር  የተባለ የጭነት ተሽከርካሪ ከዶዮገና ወደ አረካ በመጓዝ ላይ እያለ ነፍሰ ጡር ይዞ ወደ ጤና ጣቢያ በመጓዝ ላይ ከነበረ ኮድ 1-21363 ደህ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ ጋር በመጋጨቱ አደጋው ሊደርስ ችሏል። በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ  ገልጸው አስክሬናቸው  ቤተሰብ መረከቡን  አስታውቀዋል። አንድ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባት የቤተሰቡ አባል በዱቦ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት  መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የኤፍኤስ አር  አሽከርካሪ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት  እንደሚገኝም ኮማንደር  ማቲዎስ  አስረድተዋል፡፡ የአደጋው መንስኤ ለጊዜው ባይታወቅም ሲጥል የነበረው  ዝናብ   ጋር ተያይዞ    በመጋረድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የፖሊስ አዛዡ ገምተዋል። አሁን ላይ ወቅቱ ያልጠበቀ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ  አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን በመቆጣጣር ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አዛዡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም