የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ27 በመቶ አስገዳጅ ቦንድ ግዥን አነሳ

111

ኢዜአ ህዳር 12 / 2019 ዓ.ም የግል ባንኮች ለተበዳሪዎች ከሚያቀርቡት እያንዳንዱ የብድር ገንዘብ ውስጥ የ27 በመቶ ተቀናሽ አስልተው ለብሔራዊ ባንክ የቦንድ ግዥ እንዲያውሉ የሚያዝዘው መመሪያ ተነሳ።
የግል ባንኮች ለተበዳሪዎች ከሚያቀርቡት እያንዳንዱ የብድር ገንዘብ ውስጥ የ27 በመቶ ተቀናሽ አስልተው ለብሔራዊ ባንክ ቦንድ ግዥ እንዲያውሉ የሚያዝዘው መመሪያ ተነሳ።

ከባንኩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው እ.አ.አ ከ2011 ጀምሮ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረውን የ27 በመቶ አስገዳጅ ቦንድ መመሪያ ባንኩ አሁን ላይ ማንሳት እንዳስፈለገው አምኜበታለሁ ብሏል።

ይህ የአስገዳጅ የቦንድ ግዢ መመሪያ በወቅቱ ተግባራዊ ሲደረግ ከግል ንግድ ባንኮች በዚህ መልኩ የሚሰበሰበውን ገንዘብ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል መንግስት በፖሊሲ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች ብድር እንዲቀርብ በማለም ነበር።

በዚህ መልኩ የሚሰበሰበው ብር ውጤታማነቱ ላይ ጥያቄ ቢቀርብም መንግስት ግን ቅድሚያ እሰጣቸዋለሁ ለሚላቸው ዘርፎች ብድርን ለማቅረብ በቢሊየን የሚቆጠሩ ብሮችን ሰብስቧል።

በመመሪያው መሰረትም አምስት ዓመት የሞላው እያንዳንዱ ቦንድ ለግል የንግድ ባንኮቹ እስከነ ወለዱ ሲመለስላቸው ቆይቷል።

ሆኖም ግን በመመሪያው ላይ ከግል የንግድ ባንኮች በኩል በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየ እንደሆነም ይታወሳል።

የቅሬታው አንዱ መነሻም የግል ባንኮቹ ቦንዱን ከብሄራዊ ባንክ ሲገዙ የሚታሰብላቸው ወለድ ከወቅቱ የወለድ ምጣኔ በታች ሆኖ በመቆየቱ ነው።

እንዲሁም “ የግል ባንኮቹ ለቦንድ ግዢ የምናውለውን ገንዘብ ለሌላ ተበዳሪ ብንሰጥ የተሻለ ትርፍ እናገኝበት ነበር” ሲሉም ይደመጣሉ።

ብሄራዊ ባንክ ለዚህ የግል ባንኮች ሲያበድሩ ከፍተኛ ወለድ የሚያስቡ በመሆኑ በዚያ ይካካሳል የሚል ምላሽ ሲሰጣቸው መቆየቱም ይታወሳል።

በመሆኑም ባንኩ አዲስ ያወጣውና የቀድሞውን የሚሽረው መመሪያም ከኅዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ መዋሉ ነው የተገለጸው።

አዲሱ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በቀድሞው መመሪያ መሠረት በሂደት ላይ የነበሩ ተግባራት በቀድሞው መመሪያ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናሉ ተብሏል።