ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

89
ኢዜአ፤ ህዳር 10/2012 ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በመካከላቸው  ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር የመግባቢያ  ስምምነት ተፈራረሙ። የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የመከላከያ ጉዳዮች ሚኒስትር መሐመድ ቢን አህመድ አል ቦዋርዲ ናቸው የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት። በስምምነቱ ወቅትም የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ፤ ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር የሁለቱን ሀገራት ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ገልፀዋል። የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የመከላከያ ጉዳዮች ሚኒስትር መሃመድ ቢን አህመድ አል ቦዋርዲ በበኩላቸው፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመው ስምምነት ሀገሪቱ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር ያላት የትብብር አካል ነው ማለታቸውን የኢሚሬትስ ዜና አገልግሎት መረጃ ያመለክታል። የሁለትዩሽ የመከላከያ እና ወታደራዊ ትብብር ስመምነቱ በዱባይ እየተካሄደ ካለው 16ኛው የጦር አውሮፕላኖች ትርኢት ጎን ለጎን ነው የተፈረመው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም