በመቐለ የቢስክሌት ውድድር መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግና ብሩህ ተስፋ አሸነፉ

64
መቐለ ኅዳር 07 / 2012 በመቐለ ለአንድ ሳምንት በተካሄደው ዓመታዊ ክለቦች የቢስክሌት ውድድር በሴቶች መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ በወንዶች በብሩህ ተስፋ የበላይነት ተጠናቀቀ። የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ክለብ ተወዳዳሪዎች በከተማ 70 ኪሎ ሜትር የዙርና 80 ኪሎ ሜትር በረሃ፣የዳገትና ቁልቁለት የሚሸፍኑ ውድድርሮችን በማሸነፍ ነው። ብሩህ ተስፋ ክለብ ደግሞ በወንዶች የተካሄደውን 160 ኪሎ ሜትር ርቀት የደርሶ መልስ ውድድር በማሸነፍ አንደኛ ወጥቷል። በሴቶች በተደረገው ውድድር ትራንስ ኢትዮጵያና መሰቦ ክለቦች ሁለተኛ ሶስተኛ ወጥተዋል። በወንዶች የተደረገው ውድድር ጉናና ትራንስ ኢትዮጵያ ክለቦች የሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃዎችን በመያዝ አጠናቀዋል። በሁለቱም ፆታዎች በማውንቴን ቢስክሌት ከ40 እስከ 70 ኪሎ ሜትር በሸፈኑት የከተማ ዙርና የበረሃ ውድድሮች በሴቶች መቐለ 70 እንደርታ፣በወንዶች ደስታ አልኮል ክለቦች አሸንፈዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም