ቼክ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ ገለጸች

103
ህዳር 3/2012 የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የገቡትን የቼክ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ቶማሽ ፐትሪሸክን  በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። ቼክ በአፍሪካ ውስጥ ለስትራቴጅካዊ አጋርነት አድርጋ ከመረጠቻቸው ሁለት አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ መሆኗን የቼክ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ቶማሽ ፐትሪሸክን  ተናግረዋል፡፡ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር  ቶማሽ ፐትሪሸክ የቼክ ባለሀብቶችን በመምራት በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በመምጣታችው አመስግነዋል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረትና የበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዋና መቀመጫ በመሆኗ ቼክ በአፍሪካ አህጉር ለሚኖራት ግንኙነት ኢትዮጵያን እንደ ዋና በር ልትጠቀም እንደምትችል ገልጸዋል። ቼክ በውሮፓ ህብረት በኩል ለኢትዮጵያ ስለምታደርገው ድጋፍም  አቶ ገዱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጥ እየተካሄደ መሆኑን ያነሱት  አቶ ገዱ የቼክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በመንግስት በኩል ድጋፍ እንዲደርግላቸው ጠይቀዋል። የሁለቱን አገሮች ግንኙነት በኢኮኖሚው ዘርፍ ይበልጥ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ፍላጎቷ መሆኑንም  ገልጸዋል። የቼክ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶማሽ ፐትሪሸክ በበኩላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ከተመረጡ ጀምሮ የመጀመሪያው የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ ማድረጋቸውን እና በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል ሰላም ተሸላሚ በመሆናቸውም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የቼክ መንግስት የግል ባለሀብቱን የኢንቨስተመንት ተሳትፎ በማሳደግ ከ30 ዓመት በላይ የካበተ ልምድ እንዳለው ያነሱት ሚኒስትሩ በዘርፉ ለኢትዮጵያ ልምድ ለማካፈል እንደሚቻል ገልጸዋል። ቼክ በአፍሪካ ውስጥ ለስትራቴጅካዊ አጋርነት አድርጋ ከመረጠቻቸው ሁለት አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ መሆኗን በመግለጽ፣ ቼክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ ለማጠናከር ትሰራለች ብለዋል። ቼክ እና ኢትዮጵያ በትምህርት፣ በግብርና እና በትራንስፖርት ዘርፎች ይበልጥ በትብብር ለመስራት እንደሚችሉ እምነታቸው መሆኑንም  ሚኒስትሩ አብራርተዋል። የሁለቱን አገሮቸ ግንኙነት ለማጠናከር የመሪዎቸ ጉብኝት የራሱ ሚና ስላለው  አቶ ገዱ ቼክ ሪፐብሊክን እንዲጎበኙም ጋበዘዋል። በዛሬው ጉብኝታቸው በኢትዮ ቼክ የቢዝነስ ፎርም የሚሳተፉ የቼክ ባለሀብቶችን መርተው መምጣታቸውን በማስትወሰ፣ ባለሀብቶች ከኢትዮጵ አቻወቻው ጋር በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ መድረኰችም ሁለቱ አገሮች በሰብአዊ መብት እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር መስራት አንደሚችሉ  ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እና ቼል ሪፐብለክ የሁለትዮሽ ግንኙነት የመሰረቱት በ1940 ዓም ቼክ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ በከፈተችበት ወቅት ነው። አትዮጵያ በ1978 ዓም በቼክ ዋና ከተማ ፕራክ ኤምባሲዋን ከፍታ ነበረ ቢሆንም ከ1984 ዓም ጀምሮ ደረጃውን በክብር ቆንስላ ደረጃ ዝቅ በማድረግ ግንኙነታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። (የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም