ፖሊስ በሰሜናዊ ግሪክ በጭነት መኪና ሲጓዙ የነበሩ 41 ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አዋለ

114

ኢዜአ፤ ጥቅምት 25/2012 በሰሜናዊ ግሪክ አብዛኛቹ ዜግነታቸው አፍጋኒስታናዊ የሆኑ 41 ስደተኞች በጭነት መኪና ውስጥ በኮንቴነር ተሸሽገው ሲጓዙ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ከስደተኞቹ መካከል ቢያንስ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት  የመተንፈስ ችግር ያጋጠማቸው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ስምንቱ በሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸዋል።

የፖሊስ ባለስልጣናት እንደተናገሩት በጭነት መኪናው ውስጥ  ምንም አይነት ማቀዝቀዣ አልነበረም ፡፡

ስደተኞቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ዣንዚ በተባለች ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ሲሆን አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል።

የ 40 ዓመቱ የጆርጂያ የጭነት መኪና አሽከርካሪ የቡልጋሪያ  የፈቃድ ወረቀት  ይዞ እንደነበር ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓትም ፖሊስ ጉዳዩን በማጣራት ላይ ሲሆን፤ ተሽከርካሪው ከቱርክ ሳይነሳ እንዳልቀረ አመላካች ፍንጮች መኖራቸውን የግሪክ ፖሊስ ቃል አቀባይ ልትኮል ቴዎድሮስ ክሮኖፖሎስ ገልፀዋል ሲል የዘገበው ሲጂቲኤን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም