ዚምባብዌ  በመጪው ህዳር አዲስ የገንዘብ ኖት አገልግሎት ላይ ታውላለች

64
ኢዜአ ፤ጥቅምት 19/2012 የዚምባብዌ ባንክ አዲስ የዶላር ኖቶችንና ሳንቲሞችን  በህዳር ወር አገልግሎት እንደሚያውል የሀገሪቱ ማእከላዊ ባንክ  ገዥ ጆን ማንጉድያ  ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም ከሳንቲሞች በተጨማሪ 5 እና 2 የዚምባብዌ ዶላር በስርጭት ላይ እንደሆነም ተገልጿል። እ.ኤ.አ. ከ 2009 እስከ የካቲት 2019 ዚምባብዌ  የተለያዩ  የገንዘብ ስርዓትን  የሚትጠቀም ሲሆን የአሜሪካ ዶላርን እንደ ዋና መገበያያ ገንዘብ ስትጠቀም እንደነበር ተጠቅሶ፤  የዚምባብዌ  ገንዘብ አገልግሎት ላይ እንዲውል ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ  ግን መቋረጡ  ነው የተነገረው። አዲሱ የዚምባብዌ ዶላር ዋጋ ቀስበቀስ እየቀነሰ መምጣቱ፤  የአገር ውስጥ የምንዛሪ መጠን ዝቅ ማለት የዚምባብዌ መንግስት ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ በአገር ውስጥ የፈጠረውን ተፅእኖ ለማሰቀረት የገንዘብ ኖቱ መቀየር አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።፡ አዲሱ ምንዛሪ በአሁኑ ሰአት አገልግሎት ላይ የሚገኙ  ኖቶችን ና ሳንቲሞችን  በመተካት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርና የዚምባብዌ የአገር ውስጥ ዶላር የሚል ስያሜ እንዲሰጠው ሃላፊዎቹ መወሰናቸውን  የሲጂቲኤን  ዘገባ ያመለክታል፡፡              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም