ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር አቢይ አህመድ ሩስያ ገቡ

106
ኢዜአ፤ጥቅምት 11/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር  አቢይ  አህመድ በመጀመሪያው የሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ፎረም ለመሳተፍ  ሩሲያ  ሶቺ ከተማ  ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከጥቅምት 23-24/2019 ለሁለት ቀናት  በሚካሄደው ፎረም ላይ ለመሳተፍ ነው ማምሻውን የሩሲያዋ ሶቺ ከተማ  የገቡት። በሩሲያና በአፍሪካ መካካል ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ግንኙነትን ማጠናከር የፎረሙ ዋነኛ ዓላማ እንደሆነ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ   ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማህማት ጋር  ነው  ማምሻውን ሩሲያ የገቡት፡፡ ከፎረሙ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፎረሙን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የወቅቱ የአፍሪካ ኀብረት ሊቀ መንበር የግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ እንደሚከፍቱት መረጃዎች ጠቁመዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም