"ዓይንና ጆሮ ለጣና"

103
ከእንግዳው ከፍያለው ጧት 12 ሰዓት ከባህርዳር ከተማ ተነስተን ጉዟችን ወደ ምስራቅ አቅጣጫ አድርግናል። ዕድሜ ጠገቡ የአባይ ድልድይ ላይ ስንደርስ የወንዙን ፍሰት በመኪናው መሰኮት ተጠግቼ አየሁት። ከወትሮው በተለየ መልኩ ፍሰቱ ጨምሮ ወንዙ ከአፍ እስከ ደገፉ ሞልቶ መፍሰሱን ቀጥሏል። ምንምእንኳወቅቱጥቅምት ቢሆንምየአባይወንዝአሁንምአፈርይዞመጓዙንአለመቀነሱንየውሃውአለመጥራትያሳብቃል።ሰኔናሃምሌወርላይየጨረጨራግድብበመዘጋቱምክንያትየአባይወንዝፍሰትበመቀነሱበውስጡያሉድንጋዮችእንኳንፍጥጥብለውእየታዩነውየከረሙት። እንዳውም የወንዙን ፍሰት በአንድ አቅጣጫ ለማድረግ ሁለት እስካቬተር ገብተው ሲያጸዱ የነበሩት ሃምሌ ወር ላይ ነው። ሰኔ እና ሃምሌ ወር ላይ ግድቡን በመዝጋት ደለሉ ጣና ላይ እንዲከማች በማድረግ ውሃው በሚጠራበትና ከደለል ነጻ በሚሆንበት አሁን ላይ  ውሃውን መልቀቅ ምን ይሉታል ? ። የኛንአገርአመራርናባለሙያትዝብትየጣለውምመስራትያለበትንነገርመቼ፣እንዴትናለምንእንደሚሰራውአውቆበመርህአለመተግበሩነው።ጣናንሰኔናሃምሌገድቦዛሬመለቀቁምየዚሁችግርማሳያነውብዬእያሰብኩጉዞየንቀጥያለሁ። ምንምእንኳገናጧትላይወረታብንደርስምወንድልጅመዋያውንአያውቅምናቁርስእንብላብለንአርፈናል።ቁርሳችንበልተንናቡናጠጥተንጉዞወደጎንደርቀጥለናል። አዲስዘመንንአልፈንየድንጋይምሰሶከተራራውጥግከሚታይበትአካባቢስንደርስየመኪናችንጎማበመተንፈሱሹፌሩአቁሞ ጎማ መቀየሩንተያይዞታል።እኛምበአረንጓዴየተሸፈነናተራራማበመሆኑተማርከንአካባቢውንፎቶማንሳትእያነሳንቆየን።ጎማውንቀይሮሲጨርስተሳፈርንናጉዞወደጎንደሯማክሰኝትቀጠልን።ከማክሰኝትሳንደርስአንዲትትንሽከተማላይየተበላሸውንጎማሹፌሩሊያሰራመኪናውንአቆመ። ሰሞኑንበጎንደርአካባቢሁከትናብጥብጥእንዳለበሚዲያሲዘገብስለነበርየትአካባቢእንደሆነአንዳችንምየምናውቀውነገርየለም።ሹፌሩምጎማውንአሰርቶጉዟችንቀጠልን።ማክሰኝትልንደርስሁለትኪሎሜትርሲቀረንመኪናውአስፓልቱንለቆወደደቡብአቅጣጫአመራ። ጠጠር መንገድ በመሆኑ ተጠንቅቆ መጓዝ ይበጃል አልኩ በልቤ። ካልሆነ መኪናው ሲነጥር ከመኪናው ኮፈን ጋር ነጥሮ መጋጨት እንዳለ ከአንድ ሁለት ጊዜ አጋጥሞኛል። ከዛ በኋላ ዳር ስለነበርኩ በአንድ እጄ ከፊት ለፊቴ ያለውን ወንበር በመያዝ አደጋ እንዳይደርስብኝ እራሴን ጠብቄ እየተጓዝኩ ነው። ሌላውም እንዲሁ። ትንሿንኮረብታአልፈንብቅስንልለብዙዓመትከእንስሳትንክኪተከልክሎየተከበረመስክየመሰለአረንጓዴየለበሰወለልያለሜዳመስሎታየን።ሹፌራችንይሄየምታዩትየጣናሀይቅንየሸፈነውእምቦጭነውአረንጓዴመስሎየሚታየውአለን። ሃይቁን ለማየት አይኔ ቢያማትር ማየት እስከሚችለው ጥግ ድረስ በእምቦጭ የተሸፈነ አረንጓዴ ሜዳ እንጂ የውሃ ክፍል አልታይ ብሎኛል። እየተጠጋን ስንመጣ አሁን ወቅቱ እምቦጭ የሚያብብበት ወቅት በመሆኑ አልፎ አልፎ በነጭ፣ በሰማያዊ፣ ቀይና በሌሎች ቀለማት ፈክቶ ይታያል። የቀለማትውህዱህብርፈጥሯል።ማማርናውበትየድምቀትመሆኑቀርቶየጥፋትከሆነምን ያደርጋልአልኩበልቤ።እምቦጭምበአረንጓዴልምላሜውናበህብርፍካቱቢያምርምየጣናሃይቅንለማድረቅየተላከእርኩስመንፈስሆኖታየኝ።ሃሳቡየኔብቻሳይሆንከአካባቢውአርሶአደሮችምእውነትመሆኑንበቃለመጥይቄአረጋግጫለሁ። ዓይን ያለው ሰው የጣና ሃይቅ በአገራችን ትልቁ ሃይቅ መሆኑን አይቶ መገመት አያቅተውም። ያላየም ቢሆን ስለ ጣና ሃይቅ ታላቅነት ሳይሰማ አይቀርም። የጣና ሃይቅ ትልቅ ብቻ ሳይሆን 60 በመቶ የሚሆነው የአባይ ውሃ የሚመነጨውም ከዚሁ ሃይቅ መሆኑን ተመራማሪዎች የጻፉትን ሳያነብ የሚቀር ያለ አይመስለኝም። ካላነበበም ሲተረክ፣ ሲነገር፣ ሲወራና ሲዘመር ሳይሰማ አይቀርም ። 28 ዓይነት የአሳ ዝርያዎች በሃይቁ ውስጥ መኖራቸውን መቼም በባህርዳር፣ በጎርጎራ፣ በጎንደርና ሌሎች የአቅራቢያ ከተሞች በሚገኙ የዓሳ ዱለት፣ጥብስ፣ ኮተሌት… የተመገበ ሰው መገንዘቡ አይቀርም። ወይም ከአካባቢው ሰዎች፣ ከምሁራንና ሌሎች ሙያተኞች ጋር ሲያወሩ ሆነ በሹክሹክታ ሳይሰማ የሚቀር ያለ አይመስለኝም። ከዓሳ ዝርያዎቹ ውስጥስ 21 የሚሆኑት እንደ ዋሊያ፣ ቀይ ቀበሮ፣ የጭላዳ ዝንጀሮ፣ የሚኒሊክ ድኩላና ሌሎች የዱር እንስሳት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ መሆናቸውን መገንዘብ ተገቢ ነው።   ለዚህምሳይሆንአይቀርም “… አባይዳርነውቤቴ፣ጣናዳርነውቤቴ- አሳአበላሻላሁእንደድህነቴ” እያለጉብሉሁሉለሚወዳትናለሚያፈቅራትበዱር፣በሸንተረርናበገደሉሁሉሲዘፍንየሚውለው። በጣናሃይቅናአባይወንዝአካባቢዎችለሚገኙማህበረሰቦችምንቢያጡናቢቸገሩከቤታቸውየአሳስጋእንደማይጠፋማሳያመሆኑንስነቃሉ ያመላክታል ።ድሮየድሃምግብየነበረውአሳአሁንአሁንደግሞየዘናጭሃብታምምግብብቻሆኗል።ለምንየሃብታምምግብብቻሆነየሚለውንበዚህጽሁፍመጨረሻላይለመጥቀስይሞከራል። ከሃይቁ 13 ሺህቶንየአሳምርትበማምረትመጠቀምእንደሚቻልሰምተዋል? ለነገሩአለመባሉምንጥቅምአለው።እስካሁንበአሳአስጋሪዎችእየወጣጥቅምላይየሚውለውከአንድሺህቶንያልበለጠመሆኑንሲሰሙናሲያዩደግሞቁጭትናጸጸትይፈጥራል። ያለንን የተፈጥሮ ሃብት በአግባቡ አልምተን አለመጠቀማችን አንዱ ማሳያ ነው። የአሳ ሃብቱን በስፋት በማልማት አስግሮ መጠቀምና ወደ ውጭ መላክ ቢቻል ኖሮ አሁን ላይ ያለውን ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊየን ዶላር ከዘርፉ የሚገኝ ገቢ በብዙ እጥፍ ማሳደግ ይቻል እንደነበር መገመት አያዳግትም። ምንምእንኳተመራማሪዎችናጸሃፍትከላይየጠቀስኳቸውንማስረጃዎችጠቅሰውቢጽፉናበጥናታቸውቢያመላክቱምአሁንአሁንበጣናሃይቅላይየተጋረጠውየመጤአረምአደጋማስረጃውንተረትተረትእንዳያደርገውየሚያሰጋሆኖአግኝቼዋለሁ። በጎንደርዘሪያወረዳየሻጎመንጌቀበሌነዋሪየሆኑትአርሶአደርፈንታሁንውቤናመንጌአዱኛየሚያረጋግጡትይህንነው።ማንያርዳየቀበረ፣ማንይናገርየነበረእንደሚባለውእምቦጭየተባለውመጤአረምየተከሰተውበ2004 ዓ.ምአከባቢመሆኑንያወሳሉ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ በደንገልና ታንኳ ሃይቁ ውስጥ በመግባት አሳ በማጥመድ ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ከመመገብ አልፈው በቋንጣ መልክ እያዘጋጁ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ይሰጡ እንደነበር ተናግረዋል። የዛሬን አያርገውና ከዛም አልፎ ለአካባቢው ገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ ያገኙ ነበር። ፓፒረስ፣ጨፌናሌሎችየሳርዝርያዎችበሃይቁዳርለዳርበብዛትይበቅልስለነበርእያጨዱለከብቶቻቸውመኖበማቅረብሳይቸገሩይኖሩእንደነበርጠቅሰዋል። “ከጣናዳርየሚታጨደውንሳርየበሉላሞችወተታቸውየተትረፈረፈነበር” በማለትበቁጭትስሜትመሬትመሬቱንእያዩይገልጻሉ።ከብቶቻቸውንከሃይቁያጠጣሉ።ልብሳቸውንያጥባሉ።ይዋኛሉ።ይታጠባሉ ። አሁን ላይ ግን ሁለነገራቸውከጣናሐይቅየተዛመደእንደነበርበጸጸትስሜትበትዝታያወሳሉ። ወደ አጎራባች ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሚያደርጉት ጉዞ እንኳን በደንገልና ታንኳ በመጠቀም ያለምንም ድካምና የጸሃይ ቃጠሎ በሃይቁ ላይ ይጓጓዙ እንደነበር ነው የሚያወሱት። ይህ የተረገመ መጤ አረም በመምጣቱ ግን ዛሬ ላይ ተረት ተረት መስሎ እየታየን ነው ይላሉ አርሶ አደሮቹ። ከጥቂት ቀናት በፊት የእምቦጭ አረሙ እዚህ ጫፍ ላይ ብቻ ነበር። “እኛም እሰይ ሊጠፋልን ነው ። ይህስ ባሉት ማሽኖች በአንድ ሳምንት ማጽዳት ይቻላል። እኛም በጉልበታችን እናግዛለን ብለን ተስፋ አጭሮብን ነበር። ዛሬ ላይ ደግሞ ከየት እንደመጣ ሳይታወቅ ዓይን ማየት እስከሚችለው የርቀት ጥግ ድረስ ሃይቁ በመጤ አረሙ ተሸፍኗል ሲሉ በምሬት ይገልፃሉ ። በውሃው ሞገድ ከሌላ አካባቢ ተገፍቶ ወደዚህ በመምጣቱ ሃይቁን ማየት ከማንችልበት ደረጃ ላይ አድርሶታል። አንድ ሳምንት ጠፋ ስትል በቀጣዩ ሳምንት ሸፍኖት ታገኘዋለህ ። የመራባት አቅሙም ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት የሚጨምር በመሆኑ አስቸጋሪ ነው” በማለት ገልጸውታል። ወዲያው እንደተከሰተ በጉልበታችን አረሙን ለማስወገድ ያላደረግነው ጥረትም አልነበረም። ህጻን፣ ወጣት፣ ሴቱ ወንዱ… ጧት ጀምሮ እስከ ማታ ውሎው አረሙን በማውጣትና በመቆለል ነበር ጊዜውን ያሳለፈው። ከሁለትና ሶስት ዓመታት ወዲህ አረሙ እየገነገነ፤ የእኛ ጉልበት ደግሞ እየደከመ መጣ። ትልቅ ጠላት ነው የመጣብን። ከጠላትም ታግለህ የማታሸንፈው ሰይጣናዊ ጠላት ነው ። ጊዜየማይጥለው ፣ጊዜየማይከዳውብርቱጠላትነውያጋጠመን በማለትም የአረሙ አስቸጋሪነት ይገልፁታል ።የውጭወራሪንፊትለፊትተጋፍጠህገለህናሞተህታሸንፈዋለህ።እምቦጭግንከውጭጠላትበላይበመሆኑለመንግስትአቤትማለታችንከመቀጠል ውጪ አማራጭ አጥተንበታል ። መንግስትም የኛን አቤቱታና የምሁራኖችን ሃሳብ በማዳመጥ የተለያዩ ጥረቶችን ለማድረግ ሞክሯል። አረሙን የሚነቅሉ ማሽኖች ቢያስገባም ችግሩ ምን እንደሆነ ባናውቅም በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ ነው ለማለት ተቸግረናል። የባለሙያዎች ችግር ያለ ይመስለናል። በሆነ ባልሆነ ሰበብ እየፈጠሩ ከሚሰሩበት ይልቅ የማይሰሩበት ጊዜ ይበልጣል በማለት አርሶ አደሮቹ ያደረባቸውን ስጋት ያብራራሉ። “አታዩትም በማዳበሪያና በመስመር የዘራነው ሰብል እኮ እንደዚህ ለምልሞና አምሮ አይታይም” አሉ ጣታቸውን በእምቦጭ አረም ወደ ተወረረው የጣና ሃይቅ እያመለከቱ። አሁን ስጋታችን የኛ የአሳ፣ የወተት፣ ውሃ የመቅዳትም ሆነ እንስሳትን የማጠጣት… ሌሎች ጥቅሞች ቀሩብን ሳይሆን የጣና ሃይቅን በማድረቅ አካባቢያችን ወደ ምድረ በዳነት እንዳይቀይረው ነው የምንሰጋው ብለዋል ። በጣናሃይቅየተከሰተውንእምቦጭየተባለ መጤአረምለማስወገድሰባትማሽኖችበሽጎመንጌቀበሌናጎርጎራአካባቢዎችገብተውእንቅስቃሴእያደረጉእንደሚገኙየገለጹትደግሞየጣናሃይቅፕሮጀክትከፍተኛመካኒክናአስተባባሪመሃመድሃሰንነው። አንዱ ማሽን በጎርጎራ በኩል ሲሆን ቀሪዎቹ በሸጎ መንጌ ነው የሚገኙት። የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከሙላት ኢንጅነሪንግ ያሰራትን ጨምሮ አማጋና ካናዳ የተባሉ ሶስት የመጤ አረሙን እየነቀሉና የሚያጓጉዙ ማሽኖች አሉ። አንድ ከመሬት የተገጠመና ሁለት ደግሞ በበጋ ወቅት ውሃው ሲሸሽ ተቀጣጥለው ማሽኖቹ የነቀሉትን አረም ተቀብለው የሚያጓጓዙ ተጨማሪ ማሽኖች አሉ። አንድ ስካቬተርና ሲኖትራኮችም አረሙን ወደ ማስወገጃ ቦታ ለማድረስ የሚሰሩ አሉ። አማጋየተባለችውማሽንከሁሉምፈጣንናየነዳጅፍጆታዋምበአራትሰዓትከ25 ሊትርየማይበልጥነው።በአማጋስፖንጅፋብሪካከቻይናተገዝታመምጣቷንየመካኒክባለሙያውተናግሯል።በካናዳየሚኖሩኢትዮጵያውያንያመጧትካናዳየተሰኘችውማሽንደግሞየነዳጅፍጆታዋከፍያለናአረምየማስወገድአቅሟደግሞዝቅያለነው - ከአማጋጋርስትነጻጸር። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲና ሙላት ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ የተሰራው ማሽን ደግሞ አረሙን በማጓጓዝ ከሃይቁ አርቆ በማስወገድ ጠቀሜታው የጎላ ነው። ማሽኖችንአቀናጅቶበሙሉአቅማቸውለማሰራትየገጠመንዋናውችግርለማሽኖችማደሪያየሚሆንወደብአለመኖሩነው።በዚህምየውሃውሞገድሲጨምርማሽኖቹንገፍቶወደየብሱአውጥቶአቸውያድራል።ወደየብሱየተገፉትማሽኖችከድንጋይጋርበመጋጨትብልሽትሊያጋጥማቸውይችላል። ከዚህበተጨማሪምጧትስራለመጀመርሲታሰብሁሉንምማሽኖችተራበተራወደሃይቁውሃማክፍልበስካቬተርተገፍተውይገባሉ።አንዳንዱአካባቢለስካቬተርእንቅስቃሴምአስቸጋሪበመሆኑችግርእያጋጠመንነውሲልባለሙያውገልጿል። ከዚህበተጨማሪምየማሽኖቹየማስተግበሪያሰነድ/ማንዋል/ የላቸውም።የባለሙያዎችየደህንነትልብስ፣መድሃኒትናሌሎችአስፈላጊቁሳቁሶችአለመሟላትሌላውእያጋጠማቸውያለችግር። ከሁሉም በላይ ግን ለማሽኖቹ የሚያገለግለው መለዋወጫ ዕቃ ከውጭ የሚመጣ በመሆኑ በቀላል ብልሽት እስከ አራት ወርና አምስት ወር የሚቆሙ ማሽኖች አሉ በማለት አርሶ አደሮቹ ያነሱትን ቅሬታ ትክክለኛነት አረጋግጠዋል።   ከሙላት ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ጋር በመተባበር የተመረቱት ማሽኖች የአካባቢውን ስነ ምህዳር፣ አየር ጸባይና የችግሩን ስፋት መሰረት አድርገው የተመረቱ በመሆናቸው የእምቦጭን አረም በማስወገድ ችግር እንደሌለባቸው በባህርደር ዩንቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ተቋም መምህርና የጣና ፕሮጀክት ቴክኒካል ቡድን መሪ አቶ ዮናስ ምትኩ ይናገራሉ። የማሽኖቹበአካባቢውመመረትምበቴክኖሎጂሽግግር፣በስራእድልፈጠራ፣ለተማሪዎችየተግባርማስተማሪያበማድረግየእውቀትናክህሎትማበልጸጊያሆኖማገልገሉንጠቅሰውመንግስትምለአገርውስጥአምራቾችትኩረትእንዲሰጥበተግባርያሳየንበትፕሮጀክትነውብለዋል። የአረም ማጨጃ ማሽኗ በቀን አንድ ሺህ ሜትር ኩብ እምቦጭ መንቀልና ማጓጓዝ የምትችል ናት። ብልሽት እንኳ ቢያጋጥማት በሰራው ድርጅትና በራሳችን ባለሙያዎች በቀላሉ በመጠገን ወደ ስራ በማስገባት ለግማሽ ቀን እንኳ እንዳይቆሙ የሚያደርግ ነው። 80 ሜትር ኩብ በአንድ ጊዜ የሚያጓጓዙ ሁለት ማሽኖችን በመሬት ከተገጠመው ጋር በመቀጣጠልም ወደ ሃይቁ የውስጥ ክፍል በመግባት አረሙን ማስወገድ የሚቻልበት እድል አለ ብለዋል። ከውጭየመጡትማሽኖችዋናችግራቸውአረሙንአጽድተውከውሃውዳርነውመልሰውየሚደፉት።ይህደግሞማዕበልሲመጣተመልሶበመግባትይራባል።ዳርላይቢደርቅእንኳእየገባደለልበመሆንለሃይቁስጋትመሆኑአይቀርም። ስለዚህበአገርውስጥከተመረተውየመጓጓዟማሽንጋርበማቀናጀትበርቀት ወስዶበማስወገድየተወገደውአረምዳግምለሃይቁስጋትእንዳይሆንማድረግይቻላል። የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃማ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ልየው በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ለጣና ሃይቅ ጥበቃ ትኩረት በመስጠቱ እስከ አሁን ድረስ በአካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር፣ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲና ሌሎች ተቋማት ሲከናወን የነበረውን የእንቦጭ አረም ማስወገድ ተግባር አቀናጅቶ መምራት እንዲቻል ኤጀንሲያቸውን መቃቋሙን ይናገራሉ። ከአንድ ወር ያልበለጠ ጊዜ ያለው ኤጀንሲው በውሃ አካላት ተፋሰስ ላይ የአፈርና ውሃ እቀባ ስራዎችን በመስራት ፣ በመጤ አረም የተወረሩ ሃይቆችን ከአረሙ የጸዱ ማድረግና ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ መከላከል ፣ ለመጤ አረም ምግብ በመሆን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥረውን የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ሃይቆቹና ሌሎች የውሃ አካላት እንዳይገባ መከላከልና በውሃ አካላት ያለውን ብዝሃ ህይወት መጠበቅ ላይ አተኩሮ ለመስራት አቅዶ እንቅስቃሴ ጀምሯል ። ኤጀንሲው ገና ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተው እምቦጭ የተባለውን መጤ አረም የት የት አካባቢ በብዛት እንደሚገኝ፣ ምን ያህል የሃይቁን ክፍል እንደሸፈነና አረሙን ለማስወገድ የሚያስፈልገውን ገንዘብና የሰው ሃይል የሚያጠኑ ባለሙያዎች ተመድበው የዳሰሳና ቅኝት ጥናት በማካሄድ መረጃ የመሰባሰብ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል። ምን ያህሉ የሃይቁ ክፍል በእምቦጭ ተወሯል የሚለውን በትክክል ለመግለጽም የተሰበሰበውን መረጃ በሳይንሳዊ መንገድ የመተንተን ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። መጤአረሙበሃይቁላይምሆነበአካባቢውበሚኖረውማህበረሰብላይእያደረሰያለውተጽእኖከፍተኛበመሆኑበያዝነውበጀትዓመትበሰውሃይልናበመካኒካልዘዴለማስወገድርብርብይደረጋል።ከዚህውስጥምትኩረትየምንሰጠውበመጀመሪያበሰውሀይልተጠቅመንለማስወገድነው። በዚህምበጣናአዋሳኝበሚገኙወረዳዎችናቀበሌዎችከ80 ሺህበላይህዝብበነጻበማሳተፍከህዳር 1 ቀን 2012 ዓ.ምጀምሮከ30 እስከ 45 ቀናትበሚካሄድየዘመቻስራለማከናወንየቅድምዝግጅትስራእየተከናወነነው።በበጀትዓመቱአረሙንለማስወገድበእቅድከተያዘውውስጥ 80 በመቶየሚሆነውንበሰውሃይልለማስወገድግብተይዟል። በማሽነሪበመጠቀምደግሞ 20 በመቶየሚሆነውእምቦጭይወገዳል።ለዚህምከሰባቱማሽነሪዎችበተጨማሪጎንደርዩኒቨርሲቲያመረታትማሽንወደስራለማስገባትመታቀዱንተናግረዋል።በሃይቁየሚገኙሁሉንምማሽነሪዎችበማቀናጀትወደስራለማስገባትቴክኒካልኮሚቴበማቋቋምርክክብእንደሚደረግጠቁመውየመለዋወጫእጥረትንለመቅረፍከአገርውስጥአምራችድርጅቶችጋርበቅርበትይሰራልብለዋል። ለዚህምከአማራብረታብረትድርጅትጋርበቅርበትመስራትከተጀመረበትከቅርብጊዜወዲህየሚጠየቀውንየማሽኖችመለዋወጫዕቃበአጭርጊዜሰርቶማቅረብችሏል።በቀጣይምቅንጅታዊስራውተጠናክሮይቀጥላል። መጤ አረሙ እያደረሰ ያለው ጉዳት በወቅታዊ የፖለቲካ ውጥረት እየተረሳ ነው ለሚለው ጥያቄ ግን አቶ ዘላለም አይቀበሉትም። እንዳውም አሁን ነው ትኩረት የተሰጠው ባይ ናቸው። ምክንያቱም እስካሁን ራሱን ችሎ የሚሰራ ባለቤት የሆነ ተቋም አልነበረውም። አሁን ግን የክልሉ መንግስት በኤጀንሲ ደረጃ ተቋም አቋቋሟል ብለዋል። አሁንያለውሌላውችግርየወደብጉዳይነው።ወደብባለመኖሩማሽኖችበማዕበልእየተገፉዳርበመውጣታቸውለብልሽትእየተዳረጉነው።እስካሁንምወደቡመገንባትነበረበት።የትላይይገንባየሚለውንበባለሙያበማስጠናትወደቡንለመገንባትእንጥራለን። መስሪያቤታችንየተቋቋመውምይህንችግርበመፍታትየእምቦጭመጤአረምንለማስወገድነው።እምቦጭንለማጥፋትሌላኛውአማራጭኬሚካልመጠቀምነው።ነገርግንየጠናሃይቅጥልቀትቅርብከመሆኑናካለውሰፊብዝሃህይወትአንጻርበኬሚካልእምቦጭንየማጥፋትተግባርየአረሙብስብሳሽበመስመጥሃይቁውስጥላይበማረፍበደለልበቀላሉእንዲሞላስለሚያደርግተመራጭእንዳልሆነኤጀንሲውአስታውቋል። በመጀመሪያ በላቲን አሜሪካ መነሻውን ያደረገው እምቦጭ ዛሬ ላይ በኒውዝላንድ፣ፓፑዋ ኒው ጊኒ፣ ካምቦዲያ፣ ሉዊዚያና አሜሪካ፣ በህንድ፣ በኢትዮጵያ፣ማላዊናግብጽየሚገኙየውሃአካላትንበመውራርብዙጥፋትእያደረሰየሚገኝአደገኛአረምመሆኑየሚተወቅነው።በእኛሀገርደግሞከጣናበተጨማሪበቆቃናበሌሎችየውሃአካላትመስፋፋት ጀምሯል ። እውነትይህበሰይጣንየተመሰለውመጤአረምተወግዶአርሶአደሩእፎይታያገኝይሆን? ምንይህብቻበናይልተፋሰስየሚኖረውከ200 ሚሊየንበላይየሚቆጠርህዘብስየ60 በመቶውሃመገኛውየጣናሃይቅየተጋረጠበትንአደጋተቀልብሶእናየውይሆን? አዲስየተቋቋመውኤጀንሲእቅዱናህልሙተሳክቶየእምቦጭንመጥፋትያበስርይሆንወይስልክእንደእስከዛሬውሪፖርትይህንያህልበመቶለመቀነስ፣ቀነስን… የሚለውንውሃየማይቋጥርመረጃእየተሰጠይቀጥልይሆን።ዋናውነገርሰላም፣ዋናውነገርጤናያለውዘፋኝማንነበር።ጤናሰጥቶንእናየዋለን።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም