በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የእለት እርዳታ ስርጭት ተጀመረ ።

ጥቅምት 11/2012  በጎንደር ከተማ ዙሪያና አጎራባች ወረዳዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የእለት እርዳታ ስርጭት መጀመሩን የማእካዊ ጎንደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ መንበሩ አውደው ለኢዜአ እንደተናገሩት አስቸኳይ የእለት እርዳታው ከትናንት ጀምሮ አርባባ፤ ግንድ መጣያና አምቦ በር በተባሉ መጠለያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች እየተሰራጨ ነው፡፡ የእለት እርዳታ ስርጭቱም በመጠለያዎቹ ለሚገኙ 3ሺ 187 አባወሯዎችና ቤተሰቦቻቸው 500 ኩንታል የሚጠጋ የምግብ እህል መከፋፈሉን ገልፀዋል። በቀጣዮቹ ቀናትም ለ2ሺ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የእለት እርዳታ ማሰራጨት እንዲቻል በመጋዘን የሚገኘውን የአደጋ ጊዜ የመጠባበቂያ እህል ክምችት ወደ መጠለያ ጣቢዎቹ የማጓጓዝ ስራ እየተካሄደ ነው፡፡ በተጨማሪም በመጠለያዎቹ ለሚገኙ ህጻናት፣ አጥቢ እናቶችና ነብሰ ጡር እናቶች አልሚ ምግብን ጨምሮ የምግብ ዘይት ፣ ፓስታና ማኮሮኒ እንደሚቀርብ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ በተለይም አርባባ በተባለው መጠለያ ጣቢያ ባለፈው አመት ለተፈናቃዮች ተዘጋጅተው የነበሩትን የንጹህ መጠጥ ውሃና መጸዳጃ ቤቶችን በተሟላ መንገድ ወደ አገልግሎት ለማስገባት የሚያስችሉ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ ተፈናቃዮቹበመጠለያቆይታቸውሊገጥማቸውየሚችለውንየጤናችግርማቃለልእንዲቻልምበመጠለያዎችአቅርቢያየሚገኙየመንግስትጤናጣቢያዎችነጻየህክምናአገልግሎትየሚሰጡበትሁኔታመመቻቸቱንሃላፊውገልጸዋል፡፡        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም