የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ ልምድ ካላቸው አገሮችና ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

96

አዲስ አበባ  ጥቅምት 11/2012 የኢትዮጵያ -ቻይና የኢንዱስትሪ ኤክስፖ ዛሬ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል።

ለአምስት ቀን በሚቆየው ኤክስፖ ከቻይና የመጡ ከ46 በላይ የሚሆኑ አምራች ድርጅቶችና ኢንቨስተሮች እየተሳተፉበት ይገኛል።

በዝግጅቱላይየማምረቻመሳሪያዎችናየቴክኖሎጂውጤቶችለእይታ ቀርበዋል።

ይህንን ተከትሎ የአገር ውስጥ አምራቾች ከቻይና አምራቾች ጋር የልምድ ልውውጥ፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

የንግድናኢንዱስትሪሚኒስትርዴኤታአቶተካገብረየሱስየኢንዱስትሪዘርፉንለማሳደግልምድካላቸውአገሮችናድርጅቶችጋርበትብብርመስራትእንደሚገባተናግረዋል።

ዘርፉንለማሳደግየተለያዩአገሮችንተሞክሮበማየትየቻይናየተሻለሆኖበመገኘቱበትብብርእየተሰራእንደሆነገልጸዋል።

በትብብርመስራቱ በዘርፉየሚስተዋለውንየኢንዱስትሪግብአትአቅርቦት እጥረትንለማሻሻል፤የውጭምንዛሪእናየማምረቻማሽኖችንበቀላሉለማግኘትናአምራቾችበቂየሆነልምድእንዲያገኙአስተዋፅኦያደርጋልብለዋል።

አለም አቀፍ እውቅና ያላቸዉ አምራች ድርጅቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሲያደርጉ የንግድ ትስስሩን በማሳደግ ለዜጎች የስራ እድል እንደሚያስገኝ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዘርፉ የተሻለ ተሞክሮ ካላቸው አገሮች ጋራ እየሰራች እንደሆነ ተናግረው፤ በአጭር ጊዜ ተሞክሮውን በመውሰድ ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የተሻለ ኢኮኖሚ ካላቸው አገሮች ጎን ለመሰለፍ ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ቻይና በጤና፣ በትምህርትና በመሰረተ ልማት ግንባታ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በመስራት የተሻለ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እያደረገች እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ – ቻይና ኢንዱስትሪ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።